አያት አክሲዮን ማህበር በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የሚገኘውን ቁርጥራጭ ብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ayat-Real-Estate-logo-reportertenders

Overview

  • Category : Steels & Aluminium supply & sale
  • Posted Date : 11/07/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/26/2021

Description

አያት አክሲዮን ማህበር

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

አያት አክሲዮን ማህበር በድርጅቱ ቅጥር ግቢ የሚገኘውን ቁርጥራጭ ብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ማንኛውም ለመግዛት የሚፈልግ ድርጅት/ግለሰብ አንድ ኪሎግራም ቁርጥራጭ ብረት የሚገዛበትን በመነሻ ዋጋ ብር 40.00 (አርባ ብር) በሰም በታሸገ ኤንቮሎፕ በማሸግ ይኽ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ብቻ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 206 በር ላይ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ

  1. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  2. አሸናፊ ላልሆኑ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ግን ንብረቱን ሲረከብ ከሚከፍለው ገንዘብ ላይ ተቀናሽ ይደረግለታል፡፡
  3. የጨረታው ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስገቢያው ቀን ከተጠናቀቀ ከ 3 ቀናት በኃላ ይከፈታል፡፡
  4. አድራሻ ከመገናኛ ወደ ወሰን በሚወስደው መንገድ ወሰን ሚካኤል ቤተክርስቲያን መታጠፊያ ላይ እንገኛለን፡፡
  5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. የቁርጥራጭ ብረቱን ይዞታ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡

አያት አክሲዮን ማህበር

Send me an email when this category has been updated