ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተዘጋጀ አርማታ በማምረት እና በማቅረብ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ለዚሁ ስራ አገልግሎት የሚውል ለአርማታ ሴቲንግ ታይም ማራዘምያ የምንጠቀመዉ ሪታርደር ኬሚካል ማቅረብ ከሚችል አቅራቢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

national-premix-construction-plc-logo

Overview

 • Category : Chemicals & Reagents
 • Posted Date : 11/06/2021
 • Phone Number : 0118225392
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/23/2021

Description

  የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

የኬሚካል ግዢ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ናሽናል ፕሪሚክስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተዘጋጀ አርማታ በማምረት እና በማቅረብ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ለዚሁ ስራ አገልግሎት የሚውል ለአርማታ ሴቲንግ ታይም ማራዘምያ የምንጠቀመዉ ሪታርደር ኬሚካል ማቅረብ ከሚችል አቅራቢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ አቅራቢዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
  • የ2013 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
  • የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ከ29/02/2014 ዓ.ም. ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት በዋና ቢሮ ወሎ ሰፈር መስሪያ ቤት ከግዢና አቅርቦት ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ጨረታው 14/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ ጋራንቲ 5,000 (አምስት ሺህ) ብር በታሸገ ፖስታ ከፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ 3 ቀናት ውስጥ ዉል ተፈራርሞ ምርቱን ማስገባት አለባቸዉ ፡፡
 6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ: ጎተራ ፤ ወንጌላዊት ህንፃ ሳይደርሱ ፤ ካስ ታወር ጎን የመጽሀፍ ቅዱስ ኮሌጅ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308 ወይም 303-

ስልክ ቁጥር 0118225392/ 0930329140