የቦረን ሪል እስቴት አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

Announcement
Boran-Realestate-Logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/17/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/27/2021

Description

የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የቦረን ሪል እስቴት አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ብስራተ ገብርኤል በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

ስለዚህ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንድትገኙልን ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን፡፡

ሀ)  የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

 1. የማህበሩን የ2013 ዓ.ም. የዲሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥ፣
 2. የማህበሩን የ2013 ዓ.ም. የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማዳመጥ፣
 3. ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 4. በ2013 ዓ.ም. በተገኘ ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 5. የ2014 ዓ.ም. የውጭ ኦዲተር መምረጥና የሥራ ዋጋ መወሰን፣
 6. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ የትራንስፖርት አበል መወሰን፣
 7. የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

ለ)  የ14ኛው ድንገተኛ  ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

 1. የአክሲዮን ማህበሩን ካፒታል ለማሳደግ የዲሬክተሮች ቦርድን መግለጫ ማዳመጥ፣
 2. የአክሲዮን ማህበሩን ካፒታል ለማሳደግ የውጭ ኦዲተርን አስተያየት ማዳመጥ፣
 3. የአክሲዮን ማህበሩን ካፒታል ለማሳደግ አዲስ አክሲዮን ማመንጨት ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 4. የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

ማሳሰቢያ

 1. በጉባኤው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች ኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መመሪያ መሠረት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል(ማስክ) ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

 1. በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን ቀደም ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ በቦረን ሪል እስቴት አክሲዮን ማህበር ጽ/ቤት በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ተወካይ በመወከል ወይም
 2. ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሥልጣን ያለው ተወካይ ዋናውንና አንድ ኮፒ ከታደሰ መታወቂያ ወረቀት ጋር በዕለቱ ይዞ በመቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡

 

የቦረን ሪል እስቴት አ.ማ.

የዲሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated