የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ. ማህበር የዕቃ ግምጃ ቤት የሚገኙ ዝርዝራቸው በመጫረቻ ሠነድ ላይ የተዘረዘሩትን ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳደርሮ መሸጥ ይፈልጋል፣

Yencomand-Construction-Logo

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 11/21/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/29/2021

Description

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ

የንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ. ማህበር፣ ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ዕቃዎች

በአዲስ አበባ ቦሌ ክሬሸር (ከሰፈራ መስጊድ ወደ አይ.ሲ.ቲ በሚወስደው መንገድ ተከማችቶ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት የሚገኙ ዝርዝራቸው በመጫረቻ ሠነድ ላይ የተዘረዘሩትን ከአገልግሎት ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳደርሮ መሸጥ ይፈልጋል፣

የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከዚህ በታች በተመለከተው የኩባንያው አድራሻ በመቅረብ ብር 50.ዐዐ /ሃምሣ ብር/ በመክፈል መውሰድና መጫረት ይችላሉ፡፡ የጨረታ መወዳደሪያ ሠነዱን የገዙ ተጫራቾች፣ ዕቃው በሚገኝበት በአዲስ አበባ ቦሌ ክሬሸር (ከሰፈራ መስጊድ ወደ አይ.ሲ.ቲ በሚወስደው መንገድ) በመገኘት በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ07 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ፡፡

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋው 2ዐ% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ  (ሲ.ፒ.ኦ.) በማስያዝ  ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ ከፍሎ በቀጣዩ 15(አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን ንብረት አውጥቶ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያሸነፈበትን ዕቃ ካላወጣ ግን ኩባንያው ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Send me an email when this category has been updated