የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 6ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ

Announcement

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/21/2021
 • Phone Number : 0115575757
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/23/2021

Description

 የስብሰባ ጥሪ

ለኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ህግ ክፍል 2 አንቀጽ ቁጥር 393፣ 366፣ 367፣ 370፣ 371 እና 372 እንዲሁም በኩባንያው መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 9 እና 1ዐ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ጠቅላላ መድን አ.ማ ባለአክሲዮኖች 6ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ሐሙስ ታህሣሥ 14 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡3ዐ ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ስለሚካሔድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሠው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 • የኩባንያው የተፈረመ ካፒታል፣ ብር 997,300,000.00
 • የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል፣ ብር 997,300,000.00
 • የኩባንያው የንግድ ምዝገባ ቁጥር፣ MT/AA/3/0035454/2008

ሀ.  የ6ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 • የጉባኤውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሠየም፤የኩባንያው አድራሻ፣ ከተማ፡ አዲስ አበባ ፣ ክ/ከተማ፡  ቂርቆስ ፣  ወረዳ፡  9 ፣  የቤት ቁጥር፡  አዲስ
 1. ምልአተ ጉባዔውን ማረጋገጥ፤
 2. የጉባኤውን ፀሐፊ መምረጥ፤
 3. የስብሰባውን አጀንዳ ማፅደቅ፤
 4. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተከናወኑ የአክስዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ፣
 5. እ.ኤ.አ. 2ዐ2ዐ/21 የሥራ ዘመን የዲሬክተሮች ቦርድ አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ማፅደቅ፤
 6. እ.ኤ.አ. 2ዐ2ዐ/21 የሥራ ዘመን የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ማፅደቅ፤
 7. የ2ዐ2ዐ/21 በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ ድልድል እና ክፍፍል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 8. የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና የ2ኛ ዓመት የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሠን፤
 9. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን አመታዊ የአገልግሎት ክፍያ እና ወርሃዊ አበል መወሠን፤
 10. እ.ኤ.አ. 2ዐ21/22 የሥራ ዘመን የዲሬክተሮች ቦርድ ለማስመረጥ በአስመራጭ ኮሚቴ ተሻሽሎ የተዘጋጀ መመሪያን መርምሮ ማፅደቅ፣
 11. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማካሔድ፣

ለ.    የ3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 • የጉባኤውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሠየም፤የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ፤
 1. ምልአተ ጉባዔውን ማረጋገጥ፤
 2. የጉባኤውን ፀሐፊ መምረጥ፤
 3. የስብሰባውን አጀንዳ ማፅደቅ፤
 4. የኩባንያውን ካፒታል ስለማሳደግ በቀረበው የውሣኔ ሃሣብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 5. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፣

ማሳሰቢያ፡-

 • በጉባኤው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ባወጣው መመሪያ መሠረት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (Mask) ማድረግ እና ሌሎች ተገቢ የሆኑ ጥንቃቄዎችን መከተል ይገባቸዋል፡፡
 • ባለአክስዮኖች በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ከሆነ ቦሌ፣ አፍሪካ ጐዳና፣ ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከ15 ቀን ጀምሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
 • በኩባንያው ቀርባችሁ ውክልና የምትሠጡም ሆነ በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሠ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትሣተፉ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያሳይ የታደሠ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
 • በውል አዋዋይ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ ማስረጃውን እና ከፒውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ላይ መሣተፍ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር

ዐ115 575757/ ዐ115 58279ዐ/ ዐ115 582792/ ዐ115 582793 ይደውሉ

የዳይሬክተሮች ቦርድ

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ.

Send me an email when this category has been updated