የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት የብረት መደርደሪያ እቃዎች ያገለገሉ ፍሪጆችና ስቶቮች,ያገለገሉ ጎማዎች የብረት ጋሪዎችና ሌሎችም ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

CCRDA-Logo-Reporter-Tenders

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 11/24/2021
  • Phone Number : 0114393393
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/02/2021

Description

የተለያዩ ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማሰታወቂያ

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ47 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ የሚከተሉትን  ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተገጣጣሚ የብረት ስቶር (Flospan) ያገለገሉ የሰነድ ማስቀመጫዎች
  2. ያገለገሉ ብረታብረቶች ያገለገሉ ወንበሮችና ጠረጴዛዎች
  3. የብረት መደርደሪያ እቃዎች ያገለገሉ ፍሪጆችና ስቶቮች
  4. ያገለገሉ ጎማዎች የብረት ጋሪዎችና ሌሎችም

መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የዕቃዎቹን ዝርዝርና መመሪያ የያዘውን ሰነድ ከክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 103 ብር 100.00 ከፍሎ በመውሰድ ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላል፡፡

ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዓይነትና ብዛት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በድርጅቱ መጋዘን ውስጥ በመመልከት መጫረት ይችላሉ፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ በሙሉ በሶስት ቀናት ውስጥ ተረክቦ ማንሳት አለበት፡፡

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA)

አድራሻ፤ ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና መካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት

ስልክ 0114-393393 ወይም 0114-390322