የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ Light fitting እና Compound light and pole ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች እንደሚከተለው በዝርዝር የቀረቡትን ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-19

Overview

 • Category : Construction Machinery & Equipment
 • Posted Date : 11/24/2021
 • E-mail : INFO@dce-et.com
 • Phone Number : 0114403434
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/08/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለአላጌ ግብርና ማሰልጠኛ ማዕከል ፕሮጀክት በግብዓትነት የሚውል Light fitting እና ለመከላከያ ዋናው መስሪያ ቤት በግብአትነት የሚውል Compound light and pole ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች እንደሚከተለው በዝርዝር የቀረቡትን ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት የጨረታ ቁጥር ፕሮጀክት የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
1 Light fitting DCE/EM/141/2021 ለአላጌ ግብና ማሰልጠኛ ማዕከል ህዳር 30/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ህዳር 30/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15
2 Compound light and pole DCE/EM/142/2021 ለመከላከያ ዋናው መስሪያ ቤት ህዳር 29/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ህዳር 29/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15

 

ስለሆነም ፡-

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት፡፡
 3. አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአነድ ዓይነት ዕቃ ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግንባታ ግብዓት እና ምህንድስና ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

    አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46

ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ

ድህረ ገጽ፡- www.dce.et.com      ኢሜል:- INFO@dce-et.com