መክሊት ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ 13ኛ መደበኛ እና 8ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን

Announcement
Meklit-Microfinance-Institution-log-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/24/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/26/2021

Description

13ኛ መደበኛ እና 8ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን 

መክሊት ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ 13ኛ መደበኛ እና 8ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን  ቅዳሜ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጊዮን ሆቴል በሚገኘው ሕብረት አዳራሽ ያካሂዳል፡፡

የ13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤውን ጸኃፊ መምረጥ/መሰየም
 2. ድምጽ ቆጣሪዎችን መሰየም
 3. ምልአተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 4. አጀንዳ ማፅደቅ
 5. ለነባርና አዳዲስ ባለአክሲዮኖች የተሸጡ አክሲዮኖችን እና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት ሪፖርትን ማድመጥ
 7. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ
 8. በሁለቱም ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ
 9. በ2013 በጀት ዓመት በተገኘው ትርፍ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ
 • የውጪ ኦዲተሮችን መምረጥና ክፍያቸውን መወሰን
 • የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

የ8ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤውን ጸኃፊ መምረጥ/መሰየም
 2. ድምጽ ቆጣሪዎችን መሰየም
 3. ምልአተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 4. አጀንዳ ማፅደቅ
 5. የተቋሙን መመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል
 6. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

ስለሆነም ማንኛውም ባለአክሲዮን ከላይ በተጠቀሰው ዕለት እና ቦታ ተገኝተው እንዲሳተፉ ተቋሙ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ህጉ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ሊካሄድ 3 ቀን ሲቀረው አዲስ አበባ በሚገኘው ከቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ ወደ ቦሌ አትላስ በሚወስደው መንገድ ደጎል ህንጸ 1ኛ ፎቅ  ላይ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ቀርበው የውክልና ፎርም በመሙላት ተወካይ እንዲሰይሙ ያሳስባል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ባለአክሲዮኖች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ፖስፖርት ወይም የመንጃ ፍቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ