ሐበሻ ኮንስትራክሽን ማቴሪያልስና ልማት አ.ማ (ሐኮማል) የባለአክስዮኖች 10ኛ መደበኛ እና 14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ

Announcement

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/24/2021
 • Phone Number : 0978102699
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/27/2021

Description

 የስብሰባ ጥሪ

ሐበሻ ኮንስትራክሽን ማቴሪያልስና ልማት አ.ማ (ሐኮማል)

የባለአክስዮኖች 10ኛ መደበኛ እና 14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ

የሐበሻ ኮንስትራክሽን ማቴሪያልስና ልማት አ.ማ የባለአክስዮኖች 10ኛ መደበኛና 14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም የሚደረግ መሆኑን ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቃችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በአዲሱ የንግድ ሕግ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ ከመደረጉ ከ24 ቀናት በፊት ለባለአክስዮኖች ጥሪ ማድረግ እንደሚገባ ስለተደነገገ ስብሰባውን ሕዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ 22 ማዞርያ አካባቢ አክሱም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ትጋት የገበያ ማዕከል ህንፃ 12ኛ ፎቅ ላይ በሚገኝ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም ጥሪ የተደረገላችሁ የማኅበሩ ባለአክስዮኖች እንዲሁም በባለአክስዮኖች ውክልና  የተሰጣቸሁ አካላት በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እንድትገኙ የአክስዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

አጀንዳ

1ኛ/ የ10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ረቂት አጀንዳዎች

 • ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ
 • የዳይሬክተሮች ቦርድ አመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
 • የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥ፣
 • በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 • የውጪ ኦዲተሮችን መሾምና አበላቸውን መወሰን፣
 • በአክስዮን ማህበሩ ውስጥ የተደረጉ የአክስዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ
 • በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 • የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማፅደቅ ናቸው፡፡

2ኛ/ የ14ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ረቂቅ አጀንዳዎች

 • ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ፣
 • በነባር ባለአክስዮኖች የተደረጉ የአክስዮን ጭማሪዎችን እና የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ ላይ  ተወያይቶ ማፅደቅ፣
 • የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማፅደቅ ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ከሆነ በወኪልዎ አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም አሁን ካለው የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሺኝ የተነሳ ሁሉንም ባለአክስዮኖች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ስለማንችል እና ስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ከ100 ሰው በላይ መሰብሰብ ለጤና አስጊ በመሆኑ ባለአክስዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አግባብነት ካለው የመንግስት አካል የተሰጠ የውክልና ሰነድ ይዛችሁ ከስብሰባው ዕለት 3 ቀን ቀደም ብሎ ማህበሩ ባዘጋጀው ቅጽ ላይ ዋና ጽ/ቤታችን በሚገኝበት 22 አካባቢ አክሱም ሆቴል አጠገብ ትጋት የገበያ ማዕከል ህንፃ 9ኛ ፎቅ በመቅረብ ከዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መካከል  መወከል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የስልክ ቁጥሮቻችን 0978102699/0118 95 92 30

ሐበሻ ኮንስትራክሽን ማቴሪያልስና ልማት አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated