ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሚሆን የግብርና መገልገያዎችና ለእንሰሳት መመገቢያ ገንዳና የመኖ ማከማቻ ግንባታ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ህጋዊነት ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Send-a-Cow-Reportertenders

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/28/2021
 • Phone Number : 0116477233
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/11/2021

Description

የግብርና መገልገያዎችና የእንሰሳት መመገቢያና መኖ ማከማቻ ግንባታ ቁሳቁሶች ግዢ ጨረታ

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ  እ ኤ አ ከ 2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ  በምግብ ዋስትና፣እንሰሳት አያያዝ፣ተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ፣የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ቅነሳ እና መሰል የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡

በአሁን ሰዓት ድርጅቱ ከጀርሲ ኦቨርሲስ ኤይድ (Jersey Overseas Aid) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተገበረ ለሚገኘው “የወተት ልማት ለተሻለ ስርዓተ ምግብና ገቢ” /”Dairy for Improved Nutrition and Income”/ ለተባለው ፕሮጀክት ተጠቃሚ አርሶ አደሮች የሚሆን የግብርና መገልገያዎችና ለእንሰሳት መመገቢያ ገንዳና የመኖ ማከማቻ ግንባታ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ህጋዊነት ካላቸውና በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድርሻ በማስገባት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ መደብ /Lot / 1፦ የግብርና መገልገያ ቁሳቁሶች

ተቁ የእቃው ዓይነት መለኪያ   ብዛት
1 አካፋ ባለ ዶሮ (ኦርጅናል) በቁጥር   352
2 ዛቢያ ባለ ዶሮ (ኦርጅናል) በቁጥር   308
3 ሬክ ጣቱ ወፍራም የሆነ (አንደኛ ደረጃ) በቁጥር   66
4 የውሃ ማጠጫ (ናትራን) በቁጥር   198
5 የእጅ መዶሻ /እጀታው ብረት/ በቁጥር   66
6  መጋዝ ድግኖ በቁጥር   66
7 ሲባጎ /ባለ 2 ሚሊ.ና ባለ 100 ሜትር/ በጥቅል   44
8 ማጭድ /አልቪን/ በቁጥር   110
9 ሾድራ /ባለ አዞ ኦሪጅናል/ በቁጥር   198
10 ውሃ ልክ /ትንሹ/ በቁጥር   66
11 ባለ ሦስት ጥርስ መኮትኮቻ በቁጥር   308
12 ሜትር /ባለ 50 ሜትር/ በቁጥር   44
13 መኮትኮቻ ባለ 2 ጥርስ በቁጥር   220
14 ዶማ /ባለ አንድ ጥርስ/ በቁጥር   132
15 ጃሎ በቁጥር   88
16 ባለጎማ ጋሪ በቁጥር   44

የጨረታ መደብ / Lot / 2፦ የእንሰሳት መመገቢያ ገንዳና የመኖ ማከማቻ ግንባታ ቁሳቁሶች

ተ.ቁ የዕቃው ዝርዝር መለኪያ ብዛት
1 ቆርቆሮ-ባለፈረስ ቁጥር 392
2 ሚስማር 7 ቁጥር በፓኬት 10
3 ሚስማር 8 ቁጥር በፓኬት 10
4 ሚስማር 9 ቁጥር በፓኬት 10
5 ሚስማር 10 ቁጥር በፓኬት 10
6 የቆርቆሮ ሚስማር ባለቆብ በፓኬት 16
7 ጣውላ 2ሜ በ 25 ሴ.ሜ በቁጥር 112
8 ሸረራ 2ሜ በ 8ሴ.ሜ በቁጥር 728
 1. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትና ለ2014 ዓም የተደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 2. ተጫራቾች በጨረታ መደብ 1 እና 2 ለቀረቡ ቁሳቁሶች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በተለያየ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት የኖርባቸዋል፡፡
 3. አንድ ድርጅት በአንዱ ወይም በሁለቱም የጨረታ መደቦች መሳተፍ ይችላል፡፡
 4. የጨረታ ማስገቢያ ፖስታው ላይ የጨረታው መደብና ቁጥር መገለጽ ይኖርበታል፡፡
 5. ተጨራቾች በተጠየቁ ጊዜ ዋጋ ያስገቡለትን ቁሳቁስ ናሙና ለማሳየት ወይም ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻችሁን ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ማስገባት ይኖርባችኋል፡
 8. የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ታህሳስ 1 2014 ዓም ድረስ ባሉት 10 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡

ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ አድራሻ፡

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ

ሲ ኤም ሲ መንገድ፣ ከጊብሰን ት/ቤት ፊት ለፊት ጎልጎታ ህንጻ 7ኛ ፎቅ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ስልክ  (+251)-11-6-47-72-33/34

ወይም

ሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ

ወላይታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቦዲቲ ከተማ ከዳሞት ጋሌ ወራዳ ግብርና ጽ/ቤት ፊትለፊት /ኮንዶሚኒየም ጀርባ

ስልክ፡ +251 920174027

Send me an email when this category has been updated