አቢሲንያ ባንክ/አ.ማ/ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የሆኑ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Abissiniya-Bank-3

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 11/28/2021
 • Phone Number : 0116687186
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/09/2021

Description

አቢሲንያ ባንክ(አ.ማ)

አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የሆኑ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አባ/ዌሐ/006/2014

አቢሲንያ ባንክ/አ.ማ/ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የሆኑ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዓይነት ከዚህ በታች ቀርበዋል፡-

ተ.ቁ የዕቃው አይነት

(አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የሆኑ የቢሮ ዕቃዎች)

መለኪያ ብዛት የአንዱ ዕቃ የጨረታ

መነሻ ዋጋ

(ከተ.ጨ.እ.

ታክስ በፊት)

1 የመኪና ጎማ በቁጥር 126 በጨረታ
2 የመኪና ባትሪ በቁጥር` 46 በጨረታ
3 የውሃ ማጣርያ በቁጥር 2 በጨረታ
4 የብር መቁጠርያ ማሽን በቁጥር 10 በጨረታ
5 ፕሪንተር በቁጥር 7 በጨረታ
6 ሲስተም ዩኒት በቁጥር 24 በጨረታ
7 የሽንት ቤት ዕቃዎች ከነመገጣጠሚያ በጠቅል በጨረታ
8 ጠረጴዛ ባለ ብረት እግር በቁጥር 4 በጨረታ
9 የኮምፒዩተር ማስቀመጫ ጠረጴዛ በቁጥር 4 በጨረታ
10 ያገለገለ ምንጣፍ በቁጥር 3 በጨረታ
11 የአለሙኒየም ዘንግ በጥቅል በጨረታ
12 የኮት መስቀያ በቁጥር 5 በጨረታ
13 ላፐቶፕ በቁጥር 16 በጨረታ
14 ፓስቡክ ፕሪንተር በቁጥር 7 በጨረታ
15 ሲዲ ቴፕ ሪከርደር በቁጥር 12 በጨረታ
16 የሻወር ገንዳ በቁጥር 7 በጨረታ
17. ዩፒኤስ በቁጥር 11 በጨረታ
18. ሶላር ባትሪ በቁጥር 9 በጨረታ
19. ሰርቨር በቁጥር 34 በጨረታ
20. የተሰባበሩ ወንበሮች በጥቅል በጨረታ
21. የጀነሬተር ባትሪ በቁጥር 1 በጨረታ
22. የመደመርያ ማሽኖች በቁጥር 60 በጨረታ
23. ፋክስ ማሽን በቁጥር 5 በጨረታ
24. ትንሹ  የኮምፒዩተር ዴስክቶፕ በቁጥር 7 በጨረታ
25. ተንጠልጣይ ኤል ኢ ዲ መብራት በቁጥር 13 በጨረታ
26. ኤል ኢ ዲ መብራት በጥቅል በጨረታ
27. ስካነር በቁጥር 3 በጨረታ
28. የወረፋ መጠበቅያ ማሽኖች በቁጥር 2 በጨረታ
29. ቆርቆሮ በቁጥር 56 በጨረታ
30. የብረት በር በቁጥር 2 በጨረታ
31. ላሜራ ብረት በቁጥር 2 በጨረታ
32. ካውንተር በቁጥር 11 300
33. እምነበረድ በጥቅል በጨረታ
34. ቁርጥራጭ አሉሚንየም በጥቅል በጨረታ
35. የመስኮት ብረት በቁጥር 4 በጨረታ
36. የወንፊት ብረት በቁጥር 5 በጨረታ
37. የአሉሚንየም በር በቁጥር 19 በጨረታ
38. ቁርጥራጭ መስተዋት በጠቅል በጨረታ

ከተ.ቁ 1 – 29 ኮተቤ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ፊት ለፊት ባለው የባንኩ ህንፃ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ከተ.ቁ 30-38 ያሉት ዕቃዎች ሜክሲኮ በሚገኘው የዋናው መ/ቤት ግቢ ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ለመጫረት ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ሊገነዘቡ ይገባል:-

 1. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ከላይ በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ባንኩ በሚያዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም መሠረት ሜክሲኮ እና ኮተቤ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ማየት ይችላሉ::
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ብር 10000/አስር ሺ ብር/በP.O ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች መገናኛ 24 ቀበሌ ኮኮብ ሕንጻ ጀርባ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ በመቅረብ ብር` 100.00 (አንድ መቶ ብር) በPL54039 የባንክ ሂሳብ ቁጥር ከማንኛውም የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ በማስገባት ደረሰኙን ይዞ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ ዕቃዎቹን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ካሰፈሩ በኃላ የጨረታ ማስከበርያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ህዳር 30 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. አሸናፊው ተጫራች 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባቀረቡት ዋጋ ላይ በተጨማሪነት ይከፍላል፡፡
 5. ተጫራች ያሸነፈባቸውን ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች አየነት በሙሉ ወይም በጠቅላላ ባለበት ሁኔታ መረከብ አለበት፡፡ይህም ማለት በጨረታው ያሸነፈበት የአንዱ አይነት ዕቃ ዋጋ በዕቃው ቁጥር ብዛት ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋውን በመካፈል ዕቃውን የማንሳትግዴታ አለበት፡፡
 6. ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 8. ተጫራቾች ጨረታውን ለመጫረት ሰነዶችን ሲያስገብ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 687186 ወይም 0911 421569/0920 131864

 

Send me an email when this category has been updated