በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡ የተለያዩ ሸቀጦችን ከሚያመርቱ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ አምራች ጋር ለአንድ ዓመት በሚፀና ውል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Industrial-Inputs-Development-Enterprise-Logo-1

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/28/2021
 • Phone Number : 0113690791
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/09/2021

Description

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር (013/14)

     ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የደረጃ መስፈርት የሚያሟሉና ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡ የተለያዩ ሸቀጦችን ከሚያመርቱ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ አምራች ጋር ለአንድ ዓመት በሚፀና ውል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

 • የግድግዳና የቆርቆሮ ምስማር       (ES 95:2001)
 • የስፖንጅ ፍራሽ የተለያየ ዓይነት እና ትራስ፣
 • ፓስታና ማካሮኒ (ES 1055:2005)
 • አዮዲን የተጨመረበት የምግብ ጨው (CES 70:2017)
 • ሩዝ (ES ISO 7301፡2012) (በፍራንኮ ቫሉታ ከሚያስመጡ አቅራቢዎች)
 • የዕቃ ማጠቢያ ሳሙና (CES 120:2013)
 • የብርድ ልብስ
 • አንሶላ የተለያየ መጠን እና
 • ፎጣ

ስለዚህ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

 1. በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርቴፍኬት ያላቸው መሆን ይገባዋል፡፡
 2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ምርት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ

መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

 1. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለየብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 2. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን እና ከላይ ተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 3. ጨረታው በተመሳሳይ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት

ስልክ ቁጥር 0113690791/0113692647/0113692439

Send me an email when this category has been updated