የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሳ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ethiopian-insurance-corporation-Logo

Overview

  • Category : Spare Parts Sale & Supply
  • Posted Date : 11/28/2021
  • Phone Number : 0114392589
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/21/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሳ ከፍሎ ያስቀራቸውን ጋቢናዎች በተናጥል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ጋቢናዎቹን ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ከህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የጋቢና የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 ነው፡፡

ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ታህሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በማዕከሉ ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ፣ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራጮች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ፡፡

የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከክፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011439-2589 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 የኢትዮጵያ መድን ድርጅት  

Send me an email when this category has been updated