ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia-international-bank-logo-7

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 11/28/2021
  • Phone Number : 0115572037
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/14/2021

Description

የጨረታ ቁጥር:  ግፋማ/ንአ/002/2014

ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2014

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ 100.00 ( አንድ መቶ ) ብር በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሽያል ሴንተር ጎን ከሚገኘዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407-9-3 (ከንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል) በመውሰድ በጨረታው  መሳተፍ ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች ገርጂ ሮቤራ ቡና አካባቢ ከሚገኘው የባንኩ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታዉ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00  ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.  ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ተ.ቁ የዕቃው ዓይነት ብዛት
1 ያገለገሉ ኮምፒዩተሮች 3
2 ቶሺባ ሳተላይት ላፕቶፕ 1
3 የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ ዩፒኤሶች (UPS) 17
4 ያገለገለ ፕሪንተር 1
5 የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ እስካነሮች 4
6 የተለያዩ ያገለገሉ  የኢንተርኔት 3ጂ አፓራተስ/ሞዴም/ 1
7 ያገለገሉ ኤሌክትሪክ የሂሳብ ማሺኖች 5
8 የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የገንዘብ መቁጠሪያ እና መለያ ማሺኖች 54
9 የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ የፎቶ ኮፒ  እና ፋክስ ማሺኖች 2
10 የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ ባለመደገፊያ ተሸከርካሪ ወንበሮች 38
11 የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ ባለ አንድ መቀመጫ የእንግዳ ማረፊያ ወንበሮች 45
12 የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ ባለ ሶስት መቀመጫ የእንግዳ ማረፊያ ወንበሮች 19
13 ያገለገሉ የቢሮ ፀሐፊ መቀመጫ ወንበሮች 2
14 ያገለገለ የገንዘብ መያዣ ሳጥን 2
15 ያገለገሉ የዉኃና ካርበን ዳይኦክሳይድ የእሳት ማጥፊያ 2
16 ያገለገሉ የመተየቢያ ማሽኖች (Type writer) 2
17 ከባንኩ ቅርንጫፎች የተነቀሉ ካዎነንተሮች (በሜትር) 175.10 ሜትር
18 የተለያዬ መጠን ያላቸዉ ቁርጥራጭ አሉሚኒየሞች ባለበት
19 ከቅርንጫፎች የተነቀሉ ያገለገሉ የአሉሚኒየም ፍሬሞች ባለበት
20 ከብረት የተሠራ የፎቅ መወጣጫ 1
21 የተለያየ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ የተሽከርካሪና የሞተር ሳይክል ጎማዎች 71
22 የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች (Used Spare parts) ባለበት

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

መደበኛ ስልክ ቁጥር:- 0115-57-20-37/96   ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፡- 0912-73-64-32/0913-46-99-87/0911-69-53-48

Send me an email when this category has been updated