የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች የኤሌክትሪክ እና ጋዝ ምድጃዎች፣ ኤሌትሪክ ምጣድ፣ የዲሽ ሪሲቨር፣ ቦይለር፣ የተለያዩ ፍሪጆች፣ የሳኒተሪ ዕቃዎች፣ የጎረንዳዮ ቆርቆሮ፣ የመኪና ጎማዎች፣ የአዳራሽ ወንበሮች፣ የባለ 5 ሊትር ፕላስቲክ ጀሪካኖች እና የመሳሰሉትን ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Red-Cross-Society-logo-6

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 11/27/2021
 • Phone Number : 0114421130
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/10/2021

Description

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

የሰብዓዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች የኤሌክትሪክ እና ጋዝ ምድጃዎች፣ ኤሌትሪክ ምጣድ፣ የዲሽ ሪሲቨር፣ ቦይለር፣ የተለያዩ ፍሪጆች፣ የሳኒተሪ ዕቃዎች፣ የጎረንዳዮ ቆርቆሮ፣ የመኪና ጎማዎች፣ የአዳራሽ ወንበሮች፣ የባለ 5 ሊትር ፕላስቲክ ጀሪካኖች እና የመሳሰሉትን ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-

 1. ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ሳሪስ አደይ አበባ ድርና ማግ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው የማህበሩ ማሰልጠኛ ተቋም በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳሪስ ከአደይ አበባ በስተጀርባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም ግቢ ውስጥ በካሸር ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
 3. ተጫራቾች መግዛት የፈለጉትን ዕቃዎች የመግዣ ዋጋ 15% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም ስም በተዘጋጀ CPO ሳሪስ በሚገኘው ማሰልጠኛ ተቋም ካሸር ቢሮ በመቅረብ በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጨረታው ዕለት ከሆነ ደግሞ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን በኮድ የተሰጡትን ዕቃዎች ባሸነፉበት ዋጋ ሙሉ በሙሉ በመክፈል በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ተጫራች በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ከፍሎ ዕቃውን ካልወሰደ ያስያዘው ገንዘብ ለማህበሩ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
 5. በጨረታው በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል፡፡
 6. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም

*1541

É011-442-1130/011-440-2155/011-440-7460

አዲስ አበባ

Send me an email when this category has been updated