ተስፋ ድርጅት ለሚረዳቸው ተማሪዎች ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Hope-Enterprises-Logo-1

Overview

 • Category : Textile & Leather Products Sell & buy
 • Posted Date : 11/28/2021
 • Phone Number : 0118723619
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/04/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስአበባ ባሉን ቅርንጫፎች በትምህርት ፣ በሙያ ስልጠና እና በእለት እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ ለሚረዳቸው ተማሪዎች ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተማሪዎች ጫማዎች፡-

ተ.ቁ የጫማው አይነት መለኪያ ብዛት አይነት ምርመራ
1 ቆዳ ጫማ ሽፍን የወንድ (ቁጥር ከ23 – 36) ጥንድ 95 ጠንካራ ሶል ያለው  
2 ቆዳ ጫማ ሽፍን የሴት (ቁጥር ከ23 – 36) ጥንድ 45 ጠንካራ ሶል ያለው  
3 ሸራ ጫማ የወንድ (ቁጥር ከ37 – 45) ጥንድ 13 ጠንካራ ሶል ያለው  
4 ሰንደል ጫማ የወንድ(ቁጥር ከ24 – 45) ጥንድ 173 ጠንካራ ሶል ያለው  
5 ሰንደል ጫማ የሴት(ቁጥር ከ24 – 41) ጥንድ 175 ጠንካራ ሶል ያለው  
 1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣
 2. ስለጨረታው አፈፃጸም የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ አየር ጤና ከሚገኘው ዋናው ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ፣
 3. ተጫራቾች የሚያስገቡትን ዋጋ በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ከነሳምፕሉ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 27/3/2014 ዓ.ም ከቀኑ 10.00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባችዋል፣
 4. እያንዳንዱ ተጫራች የሚያቀርበውን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ / ቢድ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ በድርጅቱ ስም አሰርቶ እስከ ህዳር 27/2010 ዓ.ም ከቀኑ 10.00 ሰአት ድረስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሚያቀርበው ጥቅል ዋጋ 5% በታች /CPO/ የሚያቀርብ ለውድድሩ ብቁ አያደርግም፣
 5. አሸናፊ ተጫራቶች ባስያዙት ናሙና መሰረት ጫማዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፣ ከቀረበው ናሙና ውጪ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 28/3/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት  ይከፈታል
 7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሽ ፦     ተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት  

አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት 

 ስልክ ቁጥር 0118-72-36-19 /ፖ.ሣ.ቁ 30153

አዲስ አበባ

Send me an email when this category has been updated