የደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ

Announcement
Debub-global-Bank-Logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/29/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/26/2021

Description

ደቡብ ግሎባል ባንክ

Debub Global Bank

 የባ ለአክ ሲዮኖች ጠቅ ላላ ጉባኤ ጥሪ

የደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሠዓት ጀምሮ ግዮን ሆቴል ግቢ ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 የ9ኛ  መደበ ኛ  ጠቅ ላ ላ  ጉባኤ  አጀ ን ዳዎ ች

1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፤

2. የአክሲዮን ዝውውሮችና አዳዲስ አክሲዮኖች ሽያጭ ማሳወቅ፤

3. የ2020/21 ዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፤

4. የ2020/21 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፤

5. በዳይሬክተሮች ቦርድ እና በውጭ ኦዲተሮች ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

6. የ2020/21 የተጣራ ትርፍ ድልድል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

7. የተተኩ የቦርድ አባላትን ማሳወቅና ማጽደቅ

8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበል መወሰን፤

9. የውጭ ኦዲተሮች መሾምና አበላቸውን መወሰን፤

10. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፤

 የ3ኛ  አስ ቸኳይ  ጠቅላላ ጉ ባኤ  አጀ ንዳዎ ች

1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፤

2. የባንኩን መመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል

3. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ፤

4. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፤

 ማ ሳ ሰ ቢያ

 1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2014ዓ.ም ድረስ ብቻ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ ናሽናል ታወር ከሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 9ኛ ፎቅ ፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ በመቅረብ የውክልና ቅጽ በመሙላት ወይም አግባብ ባለው የመንግስት አካል የተረጋገጠ በስብሰባ ላይ ለመሳተፍና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ወይም የሞግዚትነት ማስረጃ በማቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 2. የድርጅት ተወካዮች ሥራ አስኪያጅ መሆናቸውን የሚያሳይ ወይም ድርጅቱን ወክለው እንዲገኙ የተፈቀደበት በውል አዋዋይ የተረጋገጠ ሰነድ በማቅረብ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 3. በጉባኤው ላይ በአካል  የምትገኙ  ባለአክሲዮኖችም  ሆኑ  ወኪሎች  የባለአክሲዮኑን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
 4. የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ በጉባኤው ላይ የሚገኙ ተሳታፊዎች በሙሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል/ማስክ ማድረግና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል አለባቸው፡፡

 ስ ለባ ንኩ  መግለጫ

 1. 1. አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07
 2. 2. የዋና ንግድ ምዝገባ ቁጥር KK/AA/3/0005948/206፣ የባንክ ሥራ ፈቃድ ቁጥር LLB/018/2012
 3. 3. ይህ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ቀን ድረስ የባንኩ የተፈረመ ካፒታል ብር 1,822,073,000.00 (አንድ ቢሊየን ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ሚሊየን ሰባ ሶሰት ሺህ ብር) ሲሆን የተከፈለ ካፒታል ብር1,491,114,537.62 (አንድ ቢሊየን አራት መቶ ዘጠና አንድ ሚሊየን አንድ መቶ አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ከስልሳ ሁለት ሳንቲም) ነው

የደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated