ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

Announcement
Esdros-construction-trade-and-industry-s.c-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/28/2021
 • Phone Number : 0930363910
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/05/2021

Description

የስብ ሰባ ጥሪ

ለኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9 መሠረት የባለአክሲዮኖች 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ኅዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ኮከብ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የ9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 2. የ9ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች ማጽደቅ
 3. አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖችን መቀበል
 4. የዲሬክተሮች ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መስማትና ማጽደቅ
 5. የውጭ ኦዲተር ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
 6. የ2013 በጀት ዓመት ትርፍ ላይ መወሰን
 7. የዲሬክተሮች ቦርድ አክሲዮናቸውን ያሳደጉ ነባር፣ አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖች በመወከል በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በመቅረብ እንዲፈርሙ ውክልና ስለመስጠት፣
 8. ተተኪ የቦርድ አባል ስለማጽደቅ
 9. የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አበል ማጽደቅ
 • የውጪ ኦዲተር ምርጫ ማካሔድና አበል ማጽደቅ
 • የ9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ  በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባኤው ከመካሔዱ በፊት ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የኅብረት ባንክ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ የውክልና ፎርሙን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ

0930-363-910/0975-382-620

0111-575-959/0111-260-101

በመጠቀም መደወል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮ ትእንገልጻለን፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር

የዲሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated