አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. 17ኛ መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ

Announcement
Lion-International-bank-logo-2

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/29/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/11/2021

Description

የባለአክስዮኖች 17ኛ መደበኛ እና የ6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎች የስብሰባ ጥሪ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. 17 መደበኛ እና 6ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ታህሳስ 02 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሒልተን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገኝተው በጉባኤው እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የ17 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች ፡-

 1. የስብሰባ አጀንዳዎችን ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 2. የአዳዲስ አክሲዮኖች ዝውውር ማጽደቅ፣
 3. የ2012/2013 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፣ መመርመርና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 4. የ2012/2013 የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት፣ የሀብትና ዕዳ ሚዛን እንዲሁም የትርፍና ኪሣራ መግለጫ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 5. በ2012/2013 የሒሳብ ዘመን የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣
 6. የ2013/2014 ዕቅድና በጀት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 7. የባንኩ የውጭ ኦዲተር ሹመት ማፅደቅ እና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፣
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ወርሃዊና ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
 9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሄድ፣
 10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት የአበል ክፍያ መወሰን፣
 11. የስብሰባው ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡

የ6 አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. በቀረበው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 2. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ፣
 3. የስብሰባው ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

በጉባዔው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከሶስት ቀናት በፊት ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና – ሌክስ ፕላዛ ህንጻ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የህግ መምሪያ 7ኛ ፎቅ በመቅረብ ባንኩ ለዚሁ ጉዳይ ባዘጋጀው የውክልና ቅፅ ላይ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የባለአክስዮኖች ህጋዊ ተወካዮች የውክልና ስልጣን የተሠጠበት ሕጋዊ ሰነድ ይዛችሁ በመቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

በጉባኤው በአካል የምትገኙም ሆነ በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡ ባለአክስዮኖች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላችሁ መሆኑን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፡፡

ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ ለምትቀርቡ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ተወያይቶ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች በጉባዔው ባልተገኙ አባላት ላይም የፀና ይሆናል፡፡

አንበሳ አንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ከብር 2.5 ቢልየን በላይ የተከፈለ ካፒታል ያለውና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ አዋጅ ቁጥር 67/1989 አንቀፅ 23 መሰረት በምዝገባ ቁጥር 05/2/13118/99 የተመዘገበ አክስዮን ማህበር ነው፡፡ የዋና መስሪያ ቤት – ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና – ሌክስ ፕላዛ ህንጻ – አዲስ አበባ፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!

Send me an email when this category has been updated