የአብጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ አክስዮን ማህበር እ.ኤ.አ የ2ዐ21 እና 2022 በጀት ዓመት ሂሳብ ብቃት ያላቸውን የውጭ ኦዲተር አገልገሎት በጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Auditing Related
  • Posted Date : 12/01/2021
  • Phone Number : 0113722908
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/04/2021

Description

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የአብጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ አክስዮን ማህበር እ.ኤ.አ የ2ዐ21 እና 2022 በጀት ዓመት  ሂሳብ  ብቃት ያላቸውን  የውጭ  ኦዲተር አገልገሎት በጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የኦዲት አገልግሎት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ይሆናሉ፡-

1ኛ/  የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መሥሪያ ቤት የተመዘገቡና ሕጋዊ የኦዲት ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣

2ኛ   የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

3ኛ/  የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4ኛ/  ለሂሳብ ምርመራ አገልገሎት ሥራው  ከሚጠይቁት ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ 3% በመቶ የተመሰከረለት ቼክ (CPO)  ወይም  በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ የጨረታ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፣

5ኛ/  የቴክኒካልና የፋይናንስ ጨረታ መወዳደረያ ሰነዶቻቸውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመረያ ቀን ጀምሮ  እሰከ ጥር 01, 2014  ዓ.ም  ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማሀበሩ ዋና  መ/ቤት  ለዚሁ  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

6ኛ/  ጨረታው  ጥር 01, 2014  ዓ.ም  ከቀኑ  9፡30 ሰዓት ይከፈታል፣

7ኛ/  በጨረታው  ለመወዳደር የሚፈልጉ የኦዲት አገልግሎት  ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ብር 100.00 በመክፈል መገዛት አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ለበለጠ መረጃ በሰልክ ቁጥር 0113 72 29 08 ወይም ጉርድ ሾላ ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ  ሕንፃ  ሰባተኛ ፎቅ በአካል  በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአቢጃታ-ሻላ ሶዳ አሽ አክሲዮን ማህበር

Send me an email when this category has been updated