ሀገርሰብ ሪል እስቴት አ.ማ ከ2014 – 2016 በጀት አመት ለ 3 አመት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ስራ በተፈቀደለት እና በተመሰከረለት የውጪ ኦዲተር የሂሳብ መዝገብ ለማስፈተሸ እና ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Auditing Related
  • Posted Date : 12/01/2021
  • Phone Number : 0114701360
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/14/2021

Description

ቀን ፡ 18/03/2014  

ቁጥር፡ ሀ.ሪ/00032/14

የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት ስራ) ጨረታ ማስታወቂያ

ሀገርሰብ ሪል እስቴት አ.ማ ከ2014 – 2016 በጀት አመት ለ 3 አመት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ስራ በተፈቀደለት እና በተመሰከረለት የውጪ ኦዲተር የሂሳብ መዝገብ ለማስፈተሸ እና ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተወዳዳሪዎች ሊያሟሉት የሚገባው መስፈርት

  • በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ በሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
  • የ2013 በጀት አመት ግብር ስለመክፈሉ የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል፤
  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
  • ተወካዩ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የሪል እስቴት ድርጅቶችን ሂሳብ የመረመረ፤

ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ የሚያስከፍሉትን ዋጋ፣ የሂሳብ ምርመራ ስራውን ሰርተው አጠናቀው ዘገባውን (Report) የሚያስገቡበትን ጊዜ የሚገልፅ መዘርዝር (Proposal) ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መሠረት ሰነዶቹን በታሸገ ኢንቨሎፕ ዝወትር በስራ ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- ከጨርቆስ ወደ ሪቼ በሚውስደው መንገድ ከማንዴላ የርቀት ትምህርት ዝቅ ብሎ ዞዊ ክሊኒክ አጠገብ (ግንባታ እየተካሔደ ያለበት ሳይት)

ስልክ:- 0114 701360

0930 601161

ሀገርሰብ ሪል እስቴት አ.ማ የቁጥጥር ኮሚቴ

Send me an email when this category has been updated