ወጋገን ባንክ አ.ማ. የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

Wegagen_bank-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 12/01/2021
 • Phone Number : 0115581635
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/25/2021

Description

የአክሲዮን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፍትህ ሚኒስቴር ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 141352 በሰጠው ውሣኔ መሠረት በባንኩ በአቶ አስመላሽ ወ/ማርያም ገብሬ ስም ተመዝግበው የሚገኙትን 191 አክሲዮኖች በሀራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በሀራጁ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 25 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዶቻችሁን በማቅረብ መጫረት ትችላላችሁ፡፡

ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡

 1. በጨረታው ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በመሳተፍ መግዛት ይችላል፡፡
 2. የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,000 (አንድ ሺህ) ነው፡፡
 3. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን አክሲዮኖች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ከጨረታው ቀን በፊት ራስ መኮንን ጐዳና አዲስ አበባ እስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ትሬዠሪ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ከህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሠነዶቹን በመውሰድ መሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ድረስ በዚሁ በባንኩ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ማስገባት አለባቸው፡፡
 4. ጨረታው ታህሳስ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በሚገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱትን አክሲዮኖች የመነሻ ጥቅል ዋጋ ¼ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. አንድ ተጫራች ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 7. ተጫራቾች ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ፣ ፖስፖርት ወይም ተቀባይነት ያለው ሌላ ማስረጃ ኮፒ እንዲሁም ድርጅቶች ከሆኑ የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 8. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት(15) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም፡፡
 9. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ ለባንኩ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፣
 10. በሌሎች ሕጐችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች የተደነገጉ ሕጐች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
 11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115- 58 16 35/0115-54 16 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ወጋገን ባንክ ..

Send me an email when this category has been updated