ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ የሕንፃ ግዢ አማካሪ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡

Nisir-Microfinance-Institution-s.c-logo

Overview

  • Category : Other Consultancy
  • Posted Date : 12/04/2021
  • Phone Number : 0115622371
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/20/2021

Description

ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ

የሕንፃ ግዢ አማካሪ አወዳድሮ ለመቅጠር የወጣ ማስታወቂያ

ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. በዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ደንበኛ ተኮር የሆኑ ምቹ፣ ቀልጣፋ፣ እና አዋጭ የሆኑ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል፤ አሁንም ተቋሙን በማሳደግ እና የደንበኞቹን ፍላጎት ይበልጥ ለማርካት የሚያግዙ አዳዲስ አሰራሮችን እየተገበረ ይገኛል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ለተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ ለመግዛት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጀምሯል፡፡ በመሆኑም በሕንፃ ግዢ የማማከር ሥራ ላይ የተሰማራችሁና ልምድ ያላችሁ አማካሪዎች የቴክኒካል (company profile, key personnel profile, relevant work experience, and other relevant documents) እና ፋይናንሻል ምክረ ሃሳብ ወይም ፕሮፖዛል በተለያየ ማሸጊያ በድርጁቱ ዋና መስሪያ ቤት በአካል ተገኝታችሁ እንድታስገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የአማካሪው የሥራ ድርሻ የሕንፃ ተጫራቾች እንዲያቀርቡ የሚጠበቅባቸውን የሕንፃውን ሁኔታ የሚገልፅ ዝርዝር መግለጫ (bidding document) ማዘጋጀት፤ ሕንፃዎችን በአካል መጎብኘትና መገምገም፤ የሕንፃውን ዋጋ ግምት ማውጣትና ሥራ አመራሩን ስለሕንፃ ግዥው ሂደት ማማከር ይሆናል፡፡

ምክረ ሃሳብ ወይም ፕሮፖዛል ለማስገባት የመጨረሻው ቀን፡ ታህሳስ 11፤ 2014 ዓ.ም.

አድራሻ፡ አዲስ አበባ፤ ደምበል ሲቲ ሴንተር፤ ታችኛው ወለል፤ ቢሮ ቁጥር BMS-02

ስልክ፡ +251115622371/ +251115622225

Send me an email when this category has been updated