ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ቦሌ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከኤድናሞል ሲኒማ አጠገብ በሚገኘው ሕንፃ ክፍሎች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡

The-United-Insurance-Company-Logo-Reportertenders

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 12/04/2021
 • Phone Number : 0111263434
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/21/2021

Description

የሕንፃ ክፍሎች የኪራይ ጨረታ

ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ቦሌ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከኤድናሞል ሲኒማ አጠገብ በሚገኘው ሕንፃ በአራተኛ ፎቅ ላይ 440.40 ካሬ ሜትር እና በስድስተኛ ፎቅ ላይ 517.40 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸውን ክፍሎች እንዲሁም ቃሊቲ አዲስ በመገንባት ላይ ያለው እስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘውን ሕንፃ ሶስተኛ ፎቅ ላይ 2006 ካሬ ሜትር፣በሁለተኛ ፎቅ ላይ 1003 ካሬ ሜትር እና በምድር ወለል ላይ 2006 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸውን ክፍሎች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

 1. የሕንፃውን ክፍሎች ለመከራየት የሚፈልጉ ተከራዬች ከሰኞ እሰከ ቅዳሜ ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላሉ፡፡
 2. ተከራዬች ለመከራየት የሚፈልጉትን ቦታ በካሬ ሜትር የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳያካትት በዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ ሞልተው በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡
 3. ሙሉ በሙሉ ለጨረታው የተዘጋጁትን የሕንፃ ወለሎች ለሚከራዩ ተከራዩች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች የክፍሉን የውስጥ ፓርቲሽን የሚያቀርበው ዲዛይን ከተፈቀደ በኋላ በራሱ ወጪ የሚሰራ ይሆናል፡፡
 4. ተጫራቾች ለሚከራዩት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00/ሁለት ሺ ብር/ ለሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ /The united insurance company SC/ ተብሎ በባንክ የተዘጋጀ ሲፒኦ ማሲያዝ አለባቸው፡፡ የተያዘው ገንዘብ በጨረታው አሸናፊ ለሆኑት ለሚከራዩት ክፍል ኪራይ ታሳቢ የሚደረግ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉት ተመላሽ ይሆንላቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴዎድሮስ አደባባይ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ከሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ፣ቦሌ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በምድር ወለል ላይ ከሚገኘው የሕንፃ አስተዳደር ቢሮ ወይም ከቃሊቲ ሕንፃ በመውሰድ የሚከራዩበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ የሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ሕብረት ኢንሹራንስ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
 7. ኩባንያው ስለኪራዩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-26-34-34 የውስጥ መስመር 190 መጠየቅ ይቻላል፡፡

Send me an email when this category has been updated