በፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር ሥር ለሚተዳደሩ ማስተባበሪያ ጽ/ቤትና አራቱ የመዝናኛ ማዕከላት አገልግሎት የሚውል ቀጥሎ የተመለከቱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Purchases
  • Posted Date : 12/04/2021
  • Phone Number : 0116631692
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/17/2021

Description

በፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር ሥር ለሚተዳደሩ ማስተባበሪያ ጽ/ቤትና አራቱ የመዝናኛ ማዕከላት አገልግሎት የሚውል ቀጥሎ የተመለከቱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ሎት አንድ የተለያዩ ዓይነትና መጠን /ብዛት/ ያላቸው የፅህፈት መሣሪያዎች፤
  2. ሎት ሁለት የተለያዩ ዓይነትና መጠን /ብዛት/ ያላቸው የፅዳት ዕቃዎች፤
  3. ሎት ሶስት የተለያዩ ዓይነትና መጠን /ብዛት/ ያላቸው የህትመት ውጤቶችን ሸማቾች ማህበሩ ሙያተኛን  አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

1ኛ. ተጫራቾች በጨረታው ለመከፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤

2ኛ. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና Tin No ያላቸው የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን  አለባቸው፤

3ኛ. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸው በትክክል ጽፈው ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

4ኛ. የጨረታው ሠነድ ለመውሰድ ሲመጡ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት አለባቸው፤

5ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ከአንድ በላይ መግዛት አይችሉም፤

6ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ /በሲፒኦ/ አስገብተው ደረሰኙ በፖስታው ከተው ማቅረብ አለባቸው፤

7ኛ. ከወጣው አሸናፊ በኋላ ዕቃውን ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ተመላሽ አይሆንም፤

8ኛ. ይህ የማስታወቁያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን  በአሥራ አንደኛው ቀን ዕለቱ የሥራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ደቂቃ ተጫራቾች ወይም  ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፤

9ኛ. የጨረታው ሣጥን ከታሸገና መክፈት ከተጀመረ በኋላ የሚወጣ ማንኛውም ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፤

1ዐኛ. የጨረታ ህጉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፤

11ኛ. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

                                    አድራሻ

ከቦሌ መድኃኒያለም አለፍ ብሎ ከኦሮሚያ ህንፃ ጀርባ በሚገኝ የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር 17/23 ህ/ል/ማዕከል የሰው/ኃ/ጠ/አገ ቢሮ ማስገባት ይቻላል፡፡

ለበለጠ መረጃ

 0116 63 16 92

0116 63 64 38

Send me an email when this category has been updated