ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ODAA-Integrated-Transport-S

Overview

 • Category : Tyre & Battery
 • Posted Date : 12/04/2021
 • Phone Number : 0116722278
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/24/2021

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ

ኦዳ ኢንተግሬትድ  ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ  የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ  በግልፅ  ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተጨራቾች ቦሌ  ቀበሌ 03ኦሮሚያ ህንፃ ላይ በሚገኘዉ  ኦዳ  ኢንተግሬትድ  ትራንስፖርት  አክስዮን  ማህበር 2ኛ ፎቅ ፋሲሊት ቢሮ በመምጣትያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማዎች እናቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ  ሠነድ የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ) ከፍለዉ ማስታወቂያዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
 1. በዋጋማቅረቢያ  ቅጽ  ላይ ተጫራቹ  የሰጠው  ዋጋ በሚለዉ  አምድ  ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸዉ  በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁሥራ  በኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት  አክስዮን ማህበር 2ተኛፎቅ ፋሲሊት ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባ15ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ተገኝተው ማስገባት አለባቸው፡፡
 1. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል በሰጡት ዋጋ እንዲሁም በነጠላና በጥቅል የሰጡት የዋጋ ልዩነት መካከልልዩነት ካለው አክስዮን ማህበሩ ከፍተኛውን ዋጋ በመውሰድ ያወዳድራል፡፡
 2. ተጫራቾች ለሚገዙት  የተሸከርካሪ  ጎማዎች እና ቁርጥራጭ ብረታብረቶች 10በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ  በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ስም አሰርተዉ ከመጫረቻ  ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ  ዉስጥ  ጨረታዉ ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 1. የጨረታሳጥን  ጨረታዉ  በጋዜጣ  ከወጣበትቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የስራ  ቀን  ከጠዋቱ በ4 :00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4 :15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ  ወኪሎቻቸዉ  በተገኙበትኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን  ማህበር  2ኛፎቅ  ፋሲሊት  ቢሮ  ይከፈታል ::  ሆኖም  ተጫራቾች በራሳቸዉ ምርጫ  ጨረታዉ በሚከፈትበት  ጊዜ ሳይገኙ  በመቅረታቸዉ  የጨረታዉን  አከፋፈት አያስተጓጉልም
 1. በጨረታዉአሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ  ከተገለፀለት በ 7 የስራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ  ክፍያ መክፈል ይኖርበታል :: ሆኖም ሙሉ ክፍያዉን በተጠቀሰዉ ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዘዉን የጨረታ ማስከበሪያ ለአክስዮን ማህበሩ ገቢ ይደረጋል፡፡
 2. አሸናፊተጫራች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለዉ በመክፈል እቃዎቹን ክፍያውን ከፈፀመ በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡
 3. አክስዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም  ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር 

ስልክ ቁጥር፡ 0116722278/0931609814

Send me an email when this category has been updated