የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኀበር የባለአክሲዮኖች 20ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 12/08/2021
 • Phone Number : 0116298983
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/02/2022

Description

  የስብሰባ ጥሪ

ለኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኀበር የባለአክሲዮኖች 20ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ታህሣሥ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 የባለአክሲዮኖች 20ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ረቂቅ አጀንዳዎች

 1. የማህበሩን ፀሐፊ መሰየም፤
 2. የማህበሩን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም፤
 3. ምልአተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፤
 4. የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፤
 5. እ.ኤ.አ 2020/21 ተጨማሪ አክሲዮን የገዙ እና አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
 6. የዲሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት መሥማት፤
 7. የኦዲተሮች ሪፖርት መሥማት፤
 8. በዲሬክተሮች እና በኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ውይይትና ውሳኔ፤
 9. እ.ኤ.አቆጣጠር 2020/21 የባለአክሲዮኖች የትርፍ ክፍፍል ሁኔታ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 10. የውጭ ኦዲተሮችን መሰየምና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፤
 11. የአገልግሎት ጊዜአቸውን ባጠናቀቁ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄድ፤
 12. የዕለቱን ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ፤

ማሳሰቢያ፡- በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ህጉ  አንቀፅ 366 እና 521  መሠረት ጉባኤው ከሚካሄድበት 3 ቀን በፊት ገርጂ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አጠገብ ወይም ገርጂ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አጠገብ  በሚገኘው የዋና መሥሪያ ቤቱ ጽ/ቤት መጥታችሁ የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት መወከል የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚሁ መሠረት ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን የተሰጣቸው ተወካዮችም በስብሰባው ላይ ባለአክሲዮኖችን ወክለው ለመገኘት እንደሚችሉ እናስታውቃለን፡፡ በስብሰባዉ ላይ ባላክሲዮኖችም ሆናችሁ ህጋዊ ተወካዮች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ይዛችሁ መገኘት ይጠበቅባችኋል፡፡ እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጣውን የጥንቃቄ መመሪያ አሟልታችሁ በስብሰባዉ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ኆኀተ-ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

ስልክ- 0116 29 89 83/80

0912661100

Send me an email when this category has been updated