አልፋ የትምህርትና ስልጠና አ.ማ ባለአክስዮኖች 26ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ

Announcement
Alpha-Educational-And-Training-Logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 12/08/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/02/2022

Description

የ26ኛው  የባለአክስዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

አልፋ የትምህርትና ስልጠና አ.ማ ባለአክስዮኖች 26ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ አሁድ ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ግሎባል  አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ህንፃ የስብሰባ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክስዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የማህበሩ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአክስዮን ማህበሩ 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ
 2. የ2013 በጀት ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት ማዳመጥ
 3. በውጭ ኦዲተር የሚቀርበውን የበጀት ዓመቱን የሀብትና ዕዳ ምዘና አነዲሁም የትርፍና ኪሳራ ሪፖርት ማድመጥ፡፡
 4. በተራ ቁጠር 2 አና 3 በቀረቡት ሪፖርቶች ላየ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ
 5. የ2013 በጀት ዓመት የተጣራ የትርፍ ክፍፍልን በሚመለከት የዲሬክተሮች ቦርድ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ማጽደቅ፡፡
 6. የአገልግሎት ጊዜያቸውን በጨረሱ የውጪ ኦዲተሮች ምትክ በዲሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን አዲስ የምርጫ የውሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ መወሰንና ክፍያቸውን ማጽደቅ፡፡
 7. የዲሬክተሮች ቦርድ አበልን መወሰን፡፡
 8. የ2014 በጀት ዓመት እቅድና በጀት ላይ ተወያይቶ መወሰን፡፡
 9. የዕለቱን ቃለ ጉባኤ ማጸደቅ ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ

 1. በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለ አክስዮን ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከ3 ቀናት በፊት ማህበሩ የዘጋጀውን የውክልና መስጫ ሰነድ ግሎባል አካባቢ በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 21 ቀርቦ በመፈረም ሌላ ሰው መወከል ይችላል ፡፡
 2. በውል አዋዋይ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ ማስረጃውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ላይ መሳተፍ የችላል፡፡

አልፋ የትምህርትና ስልጠና አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ፡፡

Send me an email when this category has been updated