የኤሌምቱ ኢንትግሬትድ ወተት ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር 10ኛ መደበኛ እና 7ኛ ድንገተኛ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

Announcement

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 12/08/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/01/2022

Description

የኤሌምቱ ኢንትግሬትድ ወተት ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር

10 መደበኛ እና 7 ድንገተኛ ዓመታዊ  የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

ቀን   ፡  ታህሣሥ 23/2014 ዓ.ም

ቦታ   ፡   ኦሮሞ ባሕል ማዕከል
የ10ኛ መደበኛ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ፣
 2. የአክሲዮን ዝውውር እና የባለአክሲዮኖችን ብዛት ማሳወቅና ማጽደቅ፣
 3. የዳይሬክተሮች ቦርድን ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ፣
 4. የውጭ ኦዲተሮችን 2013 በጀት ዓመት የሂሣብ ሪፖርት ማድመጥ፣
 5. በዳይሬክተሮች ቦርድ እና በውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድን የ2014 ወርሐዊ አበል ክፍያ መወሰን፣
 7. የኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅ፣
 8. የኦዲተሮችን የ2014 በጀት ዓመት ክፍያ ማጽደቅ፣
 9. የዕለቱን መደበኛ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፣

የ7ኛ ድንገተኛ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

 1. ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ፣
 2. የኩባንያውን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻልና ማጽደቅ፣
 3. የኩባንያውን የ2012 እና 2013 በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ ወደ ኩባንያው ካፒታል ማሳደግ፣
 4. የኩባንያውን የተመዘገበ ካፒታል ማሳደግ፣
 5. ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡

ማሳሰቢያ

 • ባለአክሲዮኖች ሆኑ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ስትመጡ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ እንደዚሁም የድርጅት ተወካዮች የሆናችሁ ኃላፊነታችሁን የሚያሳይ ማስረጃ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
 • በዕለቱ ጉባዔው ተወያይቶ የሚያሳልፋቸው ውሣኔዎች በጉባዔው ባልተገኙ አባላትም ላይ የፀና ይሆናል፡፡
 • በጉባኤው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ባወጣው መመሪያ መሠረት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (Mask) ማድረግ እና ሌሎች ተገቢ የሆኑ ጥንቃቄዎችን መከተል ይገባቸዋል፡፡
 • ባለአክስዮኖች በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ከሆነ ቦሌ መንገድ፣አፍሪካ ጐዳና፣ደንበል ሲቲ ሴንተር 5ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 507C በሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከ15 ቀን ጀምሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
 • በኩባንያው ቀርባችሁ ውክልና የምትሠጡም ሆነ በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሠ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድት ቀርቡ እንዲሁም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትሣተፉ ተወካዮች የተወካያችሁን ማንነት የሚያሳይ የታደሠ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድት ቀርቡ እናሳስባለን፡፡
 • በዕለቱ ጉባዔው ተወያይቶ የሚያሳልፋቸው ውሣኔዎች በጉባዔው ባልተገኙ አባላትም ላይ የፀና ይሆናል፡፡

ዳይሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated