ክቡራን የአማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) ባለአክስዮኖች በባንኩ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

Announcement
Amhara-Bank-S.C-

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 12/11/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/11/2021

Description

አማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ)

ክቡራን የአማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) ባለአክስዮኖች!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ለሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በጻፈው ደብዳቤ ባለአክስዮኖች በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው በባንኩ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

ክቡራን ባለአክስዮኖች ፊርማችሁ ባንኩን ስራ ለማስጀመር እና የባንኩ ባለአክስዮን መሆናችሁን ለማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን እያስታወቅን፣ በአዲስበባ የምትገኙም ሆነ አድራሻችሁ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሆናችሁ ባለአክስዮኖች እስካሁን ውክልና ያልሰጣችሁና ያልፈረማችሁ በሙሉ አዲስአበባ ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ መብራት ሃይል የመሰብሰቢያ አዳራሽ የባንኩ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ እንድትፈርሙ፤ ለመጨረሻ ጊዜ  ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብቻ የተራዘመ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ባለአክሲዮኖች ለፊርማ ሲመጡ፦

 • አክስዮን የገዙበትን ፎርም ዋናውንና ኮፒውን፡ ክፍያ የፈጸሙበትን የባንክ ስሊፕ ፣ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ፣ ፖስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆኑ ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቢጫ ካርድ እና ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ፤ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ወኪል ከሆኑ ውል ለመዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ዋናውን ከአንድ ኮፒ ጋር እና ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መፈረም የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን ፣ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ወኪሎች ከውክልና ማስረጃ በተጨማሪ የወካዮቻችሁን የትውልደ ኢትዮጵያዊነት ማስረጃ ቢጫ ካርድ ይዛችሁ መቅረብ ያስፈልጋል፡፡

በተጨማሪነት ሊጠየቁ የሚችሉ ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፥

 • በህፃናት ልጆቻቸው ስም አክሲዮን የገዙ ወላጆች ፤ ከወላጆች መታወቂያ በተጨማሪ አክሲዮን የተገዛለት ህፃን ወይም የተገዛላቸው የእያንዳንዱ ህፃናት ልጆች የልደት ሰርተፍኬት ወይም በፍርድ ቤት ሞግዚት የተባለበት የፍርድ ቤት ውሳኔ፤
 • አካለመጠን ያልደረሰ ልጅ ሞግዚት አካለመጠን ባልደረሰው ልጅ ስም አክሲዮን የገዙ ከሆነ ከሞግዚቱ መታወቂያ በተጨማሪ ሞግዚት የተባለበት የፍርድቤት ውሳኔ፡፡ በባንኩ ውስጥ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው በአባልነት ተመዝግቦ የሚገኝ ከሆነ የልደት ሰርተፍኬት ወይም በፍርድ ቤት የተሰጠ የሞግዚትነት ማስረጃ ያስፈልጋል፤
 • ሁለትና ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች በጋራ ለተገዛ የጋራ አክሲዮን ፈራሚ፣ ከመታወቂያ በተጨማሪ የእንደራሴነት ውል፤ ሆኖም ሁለት ሆነው ባልና ሚስት ነን ካሉ የጋብቻ ማስረጃውን አንዱ ተጋቢ በማምጣት መፈረም ይችላል፤
 • በማህበር ስም ለተገዛ የአክሲዮን ፈራሚ፤ የፈራሚውን ሹመትና ስልጣን እንዲሁም የማህበሩን ህጋዊነት የሚያሳዩ ሰነዶች (መመስረቻ ጹሁፍ ፣መተዳደሪያ ደንብ፣ የንግድ ስራ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ) ወይም በውል አዋዋይ ፊት የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና፡፡ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
 • በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎች አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ፣ ከመታወቂያ በተጨማሪ ከጣቢያ የአጃቢውን ፖሊስና የተጠርጣሪ ግለሰብ ስምን የሚገልፅ ቁጥር አዘል ደብዳቤ አጃቢ ፖሊሱ ይዞ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፤
 • ከውጪ ሀገራት በመጡ ሰነዶች (ውክልና፣ የልደት ሰርተፍኬት የጋብቻ ማስረጅ ፣የማህበራት መቋቋሚያ ሰነዶች) የሚፈረም ከሆነ ሰነዶቹ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጡ በኤጀንሲያችን የተመዘገበ መሆን አለበት፤
 • ከላይ የተዘረዘሩት መታወቂያዎች ሲቀርቡ ለዘመኑ የታደሱ፣ ፎቶ ግራፍ የተለጠፈባቸው፣ ማህተሙ በአግባቡ ያረፈባቸው፣ ስርዝ ድልዝ የሌለባቸው፣ መታወቂያውን የሰጠው ኃላፊ ፊርማ፣ ስምና ኃላፊነት በቲተር ወይም በእጅ ጽሁፍ በትክክል ያረፈባቸው መሆን አለባቸው፤

ማሳሰቢያ

 • ከዚህ ቀደም አማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) ያደረገውን ጥሪ ተቀብላችሁ ፣ በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ኤጀንሲ እንዲሁም በህግ ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ፊት ቀርባችሁ ለባንኩ አደራጆች ውክልና የሰጣችሁ ባለአክስዮኖች በወኪሎቻችሁ አማካኝነት የሚፈረምላችሁ በመሆኑ ፣ በድጋሜ ቀርባችሁ መፈረም የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 • አክስዮን በምትፈርሙበት (በምትገዙበት) ጊዜ ሙሉ ስማችሁን እና አድርሻችሁን አሟልታችሁ ያላስመዘገባችሁ ባለአስክዮኖች ፣ ከዚህ ቀደም ውክልና ብትሰጡም ባትሰጡም በግንባር ቀርባችሁ መረጃችሁን የማሟላት ግዴታ ያለባችሁ መሆኑን እናስታውቃለን። መረጃችሁ ያልተሟላ ባለአክስዮኖች ፣ መረጃችሁ እስኪሟላ ድረስ ስማችሁ በባንኩ የአክስዮን መዝገብ የማይገባ እና ባለአክስዮን ለመሆን የማትችሉ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
 • በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ከተደቀነው ስጋት አንጻር ለፊርማ በምትመጡበት ጊዜ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አድርጋችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ፣ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንድታደርጉ እናስታውቃልን፡፡

አማራ ባንክ አ.ማ.

(በምስረታ ላይ)