ኦሮሚያ ባንክ 12ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Announcement
Oromia-international-bank-logo-3

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 12/13/2021
 • Phone Number : 0115572082
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/25/2021

Description

ለኦሮሚያ ባንክ ባለአክሲዮኖች የተደረገ የስብሰባ ጥሪ

ኦሮሚያ ባንክ 12ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው መቻሬ ሜዳ የሚያካሂድ በመሆኑ፣ ባለአክሲዮኖች በተባለው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተገኝታችሁ በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የዳሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 • የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
 • የጉባኤውን ድምጽ ቆጣሪዎች መምረጥ፣
 • የአክሲዮን ግዥና ዝውውርን በማጽደቅ አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
 • የዳሬክተሮችን ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፣
 • በተራ ቁጥር 1.4 ሥር በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 • የባንኩን የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥ
 • በተራ ቁጥር 1.6 ሥር በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 • የዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈልን አስመልክቶ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
 • የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበላቸውን መወሰን፣
 • የዳሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ እና ወርሃዊ አበልን መወሰን፣
 • የመደበኛ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፣

ማሳሰቢያ፡-

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ ባለአክሲዮኖች የዜግነት እና ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ መታወቂያ ዋናውን ከአንድ ቅጂ ጋር ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ውክልናን በተመለከተ

በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በተወካዮቻቸው አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተሳታፊዎችን ቁጥር ለመመጠን ያመች ዘንድ ውክልናን በሚመለከት፣ ባለአክሲዮኖች በተወካዮቻቸው አማካይነት እንዲሳተፉ እያበረታታን ጉባኤው ከሚካሄድበት ዕለት ሶስት የሥራ ቀናት በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት እና በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላት፣ ወይንም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው የመንግስት አካል የተረጋገጠ የውክልና ሠነድ ዋናውንና አንድ ቅጂ በማቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  ኦሮሚያ ባንክ

 የዳሬክተሮች ቦርድ

አድራሻ፡- ዋና መ/ቤት፤ አፍሪካ ጐዳና ኦሎምፒያ አካባቢ ስ.ቁ 011557-20-82 ወይም 011557-20-80

Send me an email when this category has been updated