ለሞኤንኮ ሠራተኞች ክበብ አገልግሎት የሚውሉ የታሸጉ የምግብ ግብአቶች ፣ ጥራጥሬዎችና ቅመማቅመሞች,አትክልት እና ፍራፍሬዎች,ሥጋ ምርቶች እና የእንስሳ ተዋዕፆዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

Moenco-logo-1

Overview

  • Category : Food Items Supply
  • Posted Date : 12/15/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/01/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ለሞኤንኮ ሠራተኞች ክበብ አገልግሎት የሚውሉ ፣

ምድብ የሚቀርበው የእቃ ዓይነት መግለጫ
01 የታሸጉ የምግብ ግብአቶች ፣ ጥራጥሬዎችና ቅመማቅመሞች  
02 አትክልት እና ፍራፍሬዎች  
03 የሥጋ ምርቶች እና የእንስሳ ተዋዕፆዎች  

ለስድስት (6) ወራት በጨረታ አወዳድሮ  መግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም እቃዎቹን ተጫርቶ ማቅረብ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ሞኤንኮ ሠራተኛ ማህበር ጽ/ቤት በመቅረብ የእቃው ዝርዝር ያለበትን  የጨረታ ሰነድ መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ  በመውሰድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ከሰኞ- ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት እንዲሁም በጨረታው መክፈቻ ቀን  ቅዳሜ ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ሰነድ በመውሰድ የጨረታውን ፖስታ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በአንድ ምድብ እና ከዚያ በላይ መጫረት ይችላሉ፡፡ጨረታው ቅዳሜ ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ እለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞኤንኮ ሠራተኞት ማህበር ጽ/ቤት ይከፈታል ፡፡ ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር

አድራሻ ፡ ቦሌ ሐያት ሆስፒታል አጠገብ ፡፡

 ማስታወሻ ፡ – ለበለጠ መረጃ ፡ 251+8090-Ex-335 

Send me an email when this category has been updated