ካዛ የገበያ ማዕከል አ/ማ ኡራኤል አከባቢ እያስገነባ ያለውን (2B+G+12) ቅይጥ ህንጻ ሁለተኛ ዙር የህንጻውን ክፍል የመዋቅር (skeleton) የብሎኬት ግንባታ፣ልስን እና ተያያዥ ስራዎችን ልምዱ ባላቸው የህንጻ ስራ ተቋራጮች ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Construction Service & Maintenance
  • Posted Date : 12/20/2021
  • Phone Number : 0911112429
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/10/2022

Description

የህንጻ ግንባታ ስራ ጨረታ

ካዛ የገበያ ማዕከል አ/ማ ኡራኤል አከባቢ እያስገነባ ያለውን (2B+G+12) ቅይጥ ህንጻ ሁለተኛ ዙር (second phase)  የግንባታ ሂደት  ማለትም ከ5ኛ ፎቅ እስከ 12ኛ ፎቅ ያለውን የህንጻውን ክፍል  የመዋቅር (skeleton) የብሎኬት ግንባታ፣ልስን እና ተያያዥ ስራዎችን  ልምዱ ባላቸው የህንጻ ስራ ተቋራጮች  ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች BC/G3-4 እና ከዛ በላይ የሆኑ እና የ2013 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸው  እና የብቃት ማረጋገጫቸው  የታደሰ መሆን ይኖርበታል፡፡

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ) በመክፈል  ይህ ማስታወቂያ  በሪፖርተር ጋዜጣ  ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10 የካላንደር  ቀናት ውስጥ  ኡራኤል ሙሉጌታ የገበያ ማእከል  ህንጻ 6ኛ ፎቅ  ቢሮ ቁጥር 623  ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ  የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች  የጨረታ ሰነዱን  በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 21 የካላንደር ቀናት ውስጥ  ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ  እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡

ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

        ስልክ፡- :-È+251-9-11-112429/+251-9-11-685368/+251-9-11193563