የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉርድ ሾላ የሚገኘውን ዋና መስሪያ ቤቱን ህንፃ ለማስጠገን ይፈልጋል

Ethiopian-Athletics-Federation-logo-2

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 12/22/2021
 • Phone Number : 0116479794
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/04/2022

Description

ታህሳስ 12/2014 ዓ.ም

   ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉርድ ሾላ የሚገኘውን ዋና መስሪያ ቤቱን ህንፃ ለማስጠገን ስለፈለግን፡-

በዚሁ መሠረት፡-

 1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
 2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፤
 3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 2 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላው ዋጋ 5% CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
 7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
 8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

       አድራሻ፡-  ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፋክስ 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ 13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን