የሠንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር በር (የመግቢያና የመውጫ) በር ስራ አጫርቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Construction Service & Maintenance
 • Posted Date : 12/22/2021
 • Phone Number : 0922743452
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/31/2021

Description

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

  የሠንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር በር (የመግቢያና የመውጫ) በር ስራ አጫርቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 • ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የዘመኑ የንግድ እና በመስኩ የሰራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተ ፊኬትና የከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢዎች፣የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ
 • የዘመኑን የ2013 ግብር የከፈለና የግብር ማጣሪያ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ
 • በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር (PPAA)ስር የተመዘገበና የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያለው
 • ተጫራቾች የበሩን ዲዛይን ከማህበሩ ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት (መውሰድ) የሚኖርባቸው ሲሆን የበሩን ልኬት በተመለከተ ምንም እንኳን ማህበሩ የመነሻ ልኬት ያስቀመጠ ቢሆንም ተጫራቾች እራሳቸው መለካት እና ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ ማህበሩ ካስቀመጠው የመነሻ ልኬት ልዩነት ካለው ተጫራቾች በለኩት ልኬት መስራት የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡
 • በተጫራቾች የሚቀርበው ዋጋ ሙሉ የመስሪያ ዋጋ ሲሆን የእጅ ዋጋን ጭምር የሚያካትት ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች ምንም አይነት የመሰሪያ ዕቃም ሆነ አገልግሎት ከማህበሩ አይቀርብላቸውም
 • ለበር የሚስፈልገውን ሙሉ ስራ ያካትታል፡፡
 • ተጫራቾች የራሳቸው የሆነ መስሪያ ቦታ (work shop) ሊኖራቸው ይገባል
 • ጨረታው ቴኪኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ በአንድ ፖስታ በሁተኛው ፖስታ ፋይናንሽያል ኦሪጅናል እና ኮፒ መቅረብ አለበት
 • ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ቢል ቦንድ በባንክ የተመሰከረ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም የባንክ ዋስትና በማህበሩ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
 • የጨረታው ውጤት የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለፅ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ወድድር አይቀርብም
 • ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች (ተጫራቾች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጥዋቱ 2፡30-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት 7፡30-11 ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሠንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ አፓርትመንት ህንፃ ቁጥር 5 የመጀመሪያው ወለል በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት እና ተወዳዳሪዎች የጠቅላላ ዋጋውንና ስራውን ሰርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ የሚገልፅ ፕሮፖዛል በማያያዝ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይችላሉ
 • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ8ኛው ቀን ከጥዋቱ 4 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0922743452 ወይም 0911569869 ወይም0115574861 ደውለው መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን

ማሳሰቢያ

 • በሥራው ጉድለት ካጋጠመ የጉድለት ተጠያቂነት (Defect liability) 5% ከጠቅላላ ዋጋው ተቀንሶ የሚከፈል ይሆናል