ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር የአርት ሜታል እጅ ድጋፎች/Art metal hand rails/ ድዛይን መርጦ፤ዕቃ አቅርቦ የሚያመርትና ገጠማ ስራን ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Tracon-Trading-Logo

Overview

  • Category : Other Construction
  • Posted Date : 12/25/2021
  • Phone Number : 0913098889
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/07/2022

Description

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር

የአርት ሜታል በረንዳ ድጋፍ/ART METAL HAND RAILS/

ለማሰራት የወጣ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ በሚገኘው ትራኮን ሪል ስቴት ግንባታ 3B+G+22 የአፓርታማ ህንጻዎች ግንባታ እያከናወነ አሁን ወደ ማጠናቀቂያ ስራዎች እየገባ ይገኛል፡፡

በእነዚህ ህንጻዎች ላይ ላሉ በቁጥር ከ1000/አንድ ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ በረንዳዎች የአርት ሜታል እጅ ድጋፎች/Art metal hand rails/ ድዛይን መርጦ፤ዕቃ አቅርቦ የሚያመርትና ገጠማ ስራን ማሰራት ይፈልጋል፡፡አመልካቾች በተመሳሳይ የአርት ሜታል ስራ ላይ ቢያንስ ከ12 ፎቅ ያላነሰ ህንጻ የሰራና ለዚሁም የስራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤የብረት በረንዳ ድጋፍ ሰርቶ በማጠናቀቅ ልምድና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ባለሙያ ወይም ድርጅት የመረጠውን ዲዛይን የሚያሳይ ናሙና በማዘጋጀትና የሜትር ሊነየር ዋጋ በመሙላት እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡

ስለዚህ በስራው ላይ ከህንጻዎቹ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የስራ አፈጻፀም ልምድ ማቅረብ የሚችል ግለሰብ ወይም ኩባንያ፤ፕሮጀክቱ ላይ በአካል በመቅረብና ስራውን በመመልከት  እና አስፈላጊ መረጃዎችን በመውሰድ፤ ስራውን የሚከውንበትን ዲዛይን፤የእቃ አቅርቦት ምንጭ እና የገጠማ ልምድን የሚያሳይ ዶክመንትን እና ዝርዝር ዋጋ በማቅረብ መወዳደር የሚችል መሆኑን እገለፅን፤ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን ዝቅተኛ መመዘኛዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1ኛ. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው

2ኛ.ሳምፕል/ናሙና/የአርት ሜታል የበረንዳ ድጋፍ አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት

3ኛ.ቢያንስ ከ12 ፎቅ ያላነሰ ህንጻ ላይ የስራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

4ኛ. ቋሚ አድራሻ ያለውና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ታህሳስ 17/2014 ዓ.ም ተከታታይ ለ 10 የስራ ቀናት ጀሞ 1- ትራኮን ሪል ስቴት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ማመልከት ይችላል፡፡

ጀሞ 1 ሆፕ ዩኒቨርስቲ ጀርባ  –

ስልክ፡-0913098889/0989098625