ውመን ኢምፓወርመንት-አክሽን የ2021 የሒሳብ መዝገቦችን በሙሉ በገለልተኛ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 12/29/2021
 • Phone Number : 0116673255
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/06/2022

Description

ውመን ኢምፓወርመንት-አክሽን መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ እ.ኤ.አ የ2021 የሒሳብ መዝገቦችን በሙሉ በገለልተኛ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ የIPSAS የሒሳብ አመዘጋገብ ስርዓት የሚከተል መሆኑ ታውቆ ከታች በተዘረዘሩት መረጃዎች መሰረት፡

 • ድርጅቱ የ2021 የሂሳብ መዝገቦችን በሙሉ ይመለከታል፤
 • የሒሳብ ሰነዶቹ በቁጥር 100 ቦክስ ፋይል ይሆናሉ፤
 • የኦዲት ድርጅቱ ስራውን ሲያጠናቅቅ የኦዲት ሪፖርቱን እና ማነጅመንት ሪፖርት ዋና ሰነድ በአምስት ቅጅ ለድርጅቱ ያስረክባል፤
 • የተጠናቀቀ ሪፖርትም የድርጅቱን በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በመገኘት ጠቅለል ያለ መግለጫ ይሰጣል፤
 • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚጠይቀው የኦዲት መስፈርት መሰረት ያከናውናል፡፡

ከስራው አስቸኳይነት የተነሳ የኦዲት ድርጅቱ ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማለትም ቢበዛ ውል በተፈረመ አስራ አምስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅና ሪፖርቱን ማስገባት ይኖበታል፡፡

የኦዲት ድርጅቱ ማሟላት የሚጠበቀበት ሁኔታዎች

 • የታደሰ ንግድ ፈቃድ
 • የዘመኑ ግብር ስለመከፈሉ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
 • ቢያንስ በሙያው 4 አመትና ከዚያ በላይ የሰራ
 • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ
 • በአካውንቲንግና በኦዲት ቦርድ ፈቃድ ያለው

ስለዚህም ከላይ በተጠቀሰው ዝርዝር ስራዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተጠየቀውን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም የኦዲት ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ የማይመለስ የማስረጃችሁን ቅጅ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በስም በታሸገ ኢንቨሎብ በማስገባት መወዳደር የምትች መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ

ውመን ኢምፓወርመንት -አክሽን

 1. ፖስታ ሳጥን ቁጥር 101403 አዲስ አበባ
 2. በአካል በመቅረብ ለዋናው መስሪያ ቤት ማመልከት ለሚፈልጉ መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ኮከብ ህንፃ አለፍ ብሎ አመዴ መስጊድ ፊት ለፊት ቤት በህብረት የመኖሪያ ግቢ ውስጥ

ስልክ፡ ቁጥር 0116673255

አዲስ አበባ