ስታር ሳሙናና ዲተርጀንት ኢንዱስትሪዎች ኃ.የተ.የግል.ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 12/29/2021
 • Phone Number : 0114391860
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/10/2022

Description

 ግልጽ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ማስታወቂያ

ስታር ሳሙናና ዲተርጀንት ኢንዱስትሪዎች ኃ.የተ.የግል.ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ተ.ቁ የሰሌዳ ቁጥር የተሽከርካሪው አይነት የተሰራበት ዘመን የተሽከርካሪው ሞዴል የጨረታ መነሻ ዋጋ
1. አአ 03-01504 አውቶሞቢል 2001 NPR-66 298,000
2. አአ 3-39855 አይሱዙ ጃፓን 2007 NPR-66 298,000
3. አአ 3-39853 አይሱዙ ጃፓን 2007 NPR-66 298,000
4. አአ 3-37779 አይሱዙ ጃፓን 2006 NPR-66 297,000
5. አአ 3-44440 አይሱዙ ጃፓን 2007 NPR-66 297,450
6. አአ 3-27972 NPR ጃፓን የጭነት 2005 NPR-66 260,000
7. አአ 3-45023 አውቶሞቢል 1985 EE80L-EEMDSW 98,000
8. አአ 3-52255 የጭነት/ዴው ኮሪያ 1999 DAMAS 60,480
9. አአ 3-44443 አይሱዙ ጃፓን 2006 NPR-66 299,916
10. አአ 3-28511 አይሱዙ ጃፓን 2005 NPR-66 265,000
11. አአ 3-21186 አውቶቢስ /11 ሰው/ 1992 U-LH113V-SRPNS 220,000
12. አአ 3-00879 የመስክ ሬንጀር 1986  – 96,000
13. አአ 3-68990 የጭነት/ቻይና ቫን/ 2009 SY6482Q1 96,000
14. አአ 3-65726 አውቶብስ /ቻይና/ 2009 SY6482Q1 65,000
15. አአ 3-10897 አውቶብስ /ጀርመን/ 2003 MB140D 12,000
16. አአ 3-08383 አውቶቢስ 1995 TC2000 180,000
17. አአ 3-91811 የጭነት 2012 HD65 250,000
18. አአ 3-91810 የጭነት 2012 HD65 250,000

 

በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

 1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው
 2. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ (ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል)
 3. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 4. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹ ያሉበትን ቦታ ሃናማሪያም ወደ ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ ካስማ ኢንጂነሪንግ ህንፃ ጋር ባለው ቅያስ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመገኝት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ 5 ሰዓት ድረስ የጨረታው መክፈቻ ቀን በ16ኛው ቀን  ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት ሲሆን ቦታው በድርጅቱ ዋና መሰሪያቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ይሆናል የጨረታው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
 5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የስም ማዘዋወሪያ ገዥን የሚመለከትን ሰነዶች ማረጋገጫ እና መንገድትራንስፖርት ወጭዎችን በራሱ ይሽፈናል
 6. ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ የጨረታውን ሰነድ ከድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ) ገዝቶ ጨረታውን መወዳደር ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-439-18-60 / 011-439-35-17

ከሰላምታ ጋር

ድንበሩ ተፈራ

ም/ስራ አስኪያጅ