ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር FIS/01/2016 ባወጣው መመሪያ መሰረት የውጭ አገር ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለ አክሲዮኖች የተረከባቸውን አክሲዮኖች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Berhan-Insurance-logo-2

Overview

 • Category : Bank Related
 • Posted Date : 01/12/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/25/2022

Description

በድጋሚ የወጣ የአክሲዮን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር FIS/01/2016 ባወጣው መመሪያ መሰረት የውጭ አገር ዜግነት ካላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለ አክሲዮኖች የተረከባቸውን አክሲዮኖች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የአክሲዮን መለያ ኮድ የአክሲዮኖች ብዛት የአንድ አክሲዮን መነሻ ዋጋ በብር  የአክሲዮኖች ጠቅላላ የጨረታ መነሻ ዋጋ
3794 – 3833 & 81594-81597 44 1000 44,000
81618 – 81667 50 1000 50,000
81668 – 81767 100 1000 100,000
77671- 77775 105 1000 105,000
 1. ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጓቸውን አክስዮኖች ለመጫረት ዋጋ በሚያቀርቡበት ወቅት ለመግዛት የሚፈልጉትን የአክስዮን መለያ ኮድ፤ አንድ አክስዮን የሚገዙበትን ዋጋ፤ በመለያ ኮዱ የተጠቀሰውን ጠቅላላ አክሲዮን የሚገዙበትን ዋጋ የሚገልጽ በጽሁፍ በተዘጋጀ ማመልከቻ ወይም ኢንሹራንሱ ለዚሁ ዓላማ ባዘጋጀው ቅጽ በመጻፍና በኢንቨሎፕ በማሸግ እስከ ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ወሎ ሰፈር አደባባይ ጋራድ ህንፃ 7ተኛ ፎቅ ላይ የኢንሹራንሱ ዋና መሥሪያ ቤት ፋይናንስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ተግባር ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 2. ጨረታው ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት በኢንሹራንሱ ዋና መስሪያ ቤት 7ተኛ ፎቅ የቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
 3. ተጫራቾች ለመጫረት የመረጡትን የአክስዮን መለያ ኮድ በፓስታው ላይ በግልጽ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን የጠቅላላ አክስዮኖቹን መነሻ ዋጋ 1/4ተኛ መጠን የያዘ፣ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ. አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 6. ተጫራቾች የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ወይም ፓስፖርት ወይም ተቀባይነት ያለው ሌላ ማስረጃ ኮፒ እንዲሁም ድርጅቶች፤ማህበራት፤ የንግድ ተቋማት ከሆኑ ደግሞ የባለአክሲዮኖቹን ዜግነት የሚገልፅ ሰነድ እንዲሁም የመመስረቻ ጽሁፍ ወይም ተቀባይነት ያለው ሰነድ ኮፒ ከማመልከቻው/ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጹ / ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 7. በአንድ መለያ ኮድ ውስጥ የቀረቡ አክሲዮኖችን ከፋፍሎ ዋጋ ማቅረብ /መጫረት /አይቻልም፡፡
 8. የዜግነት ማስረጃ ሳይያያዝ የሚቀርብ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ማመልከቻ/ ተቀባይነት የለውም፡፡
 9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያያዘበት ወይም ከሚጠበቀው መጠን በታች የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. የቀረበበት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ማመልከቻ/ተቀባይነት የለውም፡፡
 10. የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ወይም በኢንሹራንሱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለኢንሹራንሱ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታ ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ ለሚመለከተው አካል ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ወዲያው ለተጫራቾች ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 11. የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ገቢ የሚያደርጉት በውጭ ምንዛሪ ይሆናል ፡፡ ለዚህም ሲባል ጨረታ ያሸነፉበትን ክፍያ በውጭ ምንዛሪ ከፈፀሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለአሸናፊዎች ተመላሽ ይደረጋል፡፡ ክፍያውን ካልፈፀሙ ግን የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ አይደረግም፡፡
 12. ከአንድ በላይ በሆኑ የአክሲዮን መለያ ኮዶች ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የአክሲዮን መለያ ኮድ የተለያየ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ ማመልከቻ/ በማቅረብ ለእያንዳንዱ ለሚጫረቱበት አክሲዮን በመለያ ኮዱ መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. በማያያዝ እና የዜግነት ማረጋገጫ ሰነድ በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
 13. በጨረታው ሂደትና አፈጻጽም ላይ ሊፈጠር የሚችል አለመግባባት አግባብነት ባላቸው ሕጎችና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን መመሪያዎች ተፈጻሚ በማድረግ መፍትሔ ይሰጣቸዋል፡፡
 14. ኢንሹራንሱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ወሎ ሰፈር አደባባይ ጋራድ ህንፃ 7ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የኢንሹራንሱ ዋና መሥሪያ ቤት ፋይናንስ ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች ዘወትር በስራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

Send me an email when this category has been updated