ራስ ሆቴል የማቀዝቀዣ ሩም (Cold room) ሞተር ገጠማና የማቀዝቀዣ ጋዝ የውስጥ መስመር ዝርጋታ ሥራን በብቁ ሙያተኛ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Construction Service & Maintenance
  • Posted Date : 01/12/2022
  • Phone Number : 0929248944
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/21/2022

Description

 የኮልድሩም የዕጅ ሥራ ጨረታ

 ራስ ሆቴል የማቀዝቀዣ ሩም (Cold room) ሞተር ገጠማና የማቀዝቀዣ ጋዝ የውስጥ መስመር ዝርጋታ ሥራን በብቁ ሙያተኛ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

     ይህን ሥራ ለማከናወን የሙያው ፈቃድ፣ በቂ ልምድና ችሎታ ያላቸው ሙያተኞች (ድርጅትም ሆነ ግለሰብ) ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አሥረኛው የሥራ ቀን ድረስ ስለጨረታው የሚያስረዳውን የጨረታ ሰነድ ከሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

    ተጫራቾች በአሥረኛው የሥራ ቀን ወይም ይህ ቀን በሳምንት መጨረሻ ቀናት ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በተከታዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ዋጋቸውን ያስገባሉ፣ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡

     ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0929248944 እና በ0115521202 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 ራስ ሆቴል ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

        EVERTING EXCEPT EXCESS   

  ራስ ሆቴል