ሐበሻ ቢራ አክስዮን የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን ፣ የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Habesha-Breweries-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 01/18/2022
 • Phone Number : 0911582480
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/28/2022

Description

ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር

የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች እና ማመሳሪያዎች ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሐበሻ ቢራ አክስዮን  የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችን ፣ የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. በጨርታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀረብ ለተገለጸባቸው እቃዎች ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ  ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ) በሲፒኦ ብቻ ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር  ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡
 4. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከጥር 13 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 20 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ 8፡00 ስዓት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ
 5. ጨረታው ጥር 20 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት በስራ ሰዓት ግዥ ዋና ክፍል ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡ ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፣ሙሉ አድራሻቸውን፣ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡
 6. ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር ጽ/ቤት

ቦሌ ኤድናሞል ዝቅ ብሎ ሞርኒግ ሰታር ሞል ፊት ለፊት

ስ.ቁ 0911582480 / 0967300444

አዲስ አበባ፣

ኢትዮጵያ