አባሐዋ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የሚሠሩና በብልሽት የቆሙ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Sale
- Posted Date : 01/18/2022
- Phone Number : 0114711575
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/03/2022
Description
ያገለገሉ የሚሠሩና በብልሽት የቆሙ ተሽከርካሪዎች በጫረታ
ለመሸጥ የወጣ የመጀመሪያ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ፣
ድርጅታችን አባሐዋ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ የሚሠሩና በብልሽት የቆሙ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ/ቁ | ሰሌዳ ቁጥር | ሞዴል | የመነሻ ጫራታ ዋጋ | ተሸከርካሪው ያለበት ሁኔታ |
1 | ኦሮ-03-16600 | አይቪኮ ትራክ | 880,000.00 | ያገለገለ /በብልሽት የቆመ/ |
2 | አ.አ-03-A11313 | ኪያሬኖ 1996 | 970,000.00 | ያገለገለ /በብልሽት የቆመ / |
3 | አ.አ-03-A30994 | D4D/2KD/ | 710,000.00 | ያገለገለ /በብልሽት የቆመ / |
4 | አ.አ-03-49808 | 5L | 620,000.00 | ያገለገለ /በብልሽት የቆመ / |
5 | አ.አ-03-55893 | ዳዎ ዳማስ | 310,000.00 | ያገለገለ /በብልሽት የቆመ / |
6 | አ.አ-03-98777 | ቶዮታ ቪትዝ | 570,000.00 | ያገለገለ / በስራ ላይ ያለ / |
7 | አ.አ-03-78395 | ቶዮታ ቪትዝ | 545,000.00 | ያገለገለ /በብልሽት የቆመ / |
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለቡ መብራት ኃይል ከሚገኘው አባሐዋ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ ዋናው ቢሮ ፋይናንስ ትሬዠሪ ክፍል ድረስ በመምጣት ስለጫረታው ዝርዝር መግለጫ የያዘ የጨረታ ሰነዱን ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መውሰድ እና መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ
- ጫረታው ከ19/05/14 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/5/2014 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ቆይቶ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለቡ መብራት ኃይል በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አባሐዋ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይከፈታል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ የሚሠሩና በብልሽት የቆሙ ተሽከርካሪዎችን የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ ከ19/05/14 ዓ.ም እስከ 26/5/2014 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 እና ከሠዓት ከ8፡00 – 11፡00 ሠዓት ድረስ ጨረታ የገዙበትን ሠነድ እና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት ወለቴ ከካፒታል ሲሚንቶ አጠገብ በሚገኘው ፋብሪካችን ዛኪ የፕሪፎርምና ካፕ ማምረቻ ድረስ በመምጣት ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ(ሲፒኦ) የመነሻ ጨረታ ዋጋውን 10 ፐርሠንት ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ሌሎች አስፈላጊ ዝርዝር መረጃዎች በጫረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፁ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ድርጅቱ በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114711575/0930034988 መደወል ይችላሉ፡፡
ድርጅቱ