ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተሸከርካሪዎች አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Nib-Insurance-logo

Overview

 • Category : Vehicle Purchase
 • Posted Date : 02/02/2022
 • Phone Number : 0913943333
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/16/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተሸከርካሪዎች አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 • ተሽከርካሪዎችና የተሸከርካሪ አካላት መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቆርኪ ፋብሪካ ወደ ሚድሮክ ተርሚናል በኩል በሚያልፈው አስፋልት መንገድ ገብቶ አሉሙኒየም ፋብሪካ ፊት ለፊት በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የኩባንያችን የከባድ ተሽከርካሪዎች መቆሚያ ግቢ እና ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ጀርባ መድን ዲኮር አጠገብ በሚገኘው የመለስተኛ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ግቢ (የኩባንያችን ሪከቨሪዎች) በመገኘትና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ደንበል ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ፡፡
 • በተጨማሪም ብቸና አካባቢ ሸበል በረንታ ወረዳ አባይ ሸለቆ ገደል ውስጥ የሚገኘውን ኤክስካቫተር ሠ.ቁ ሥከ-EX-2251 ባለበት ቦታና ሁኔታ በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ዋናው መ/ቤት ወይም ባህርዳር ቅርንጫፋችን በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918- 066413 ይደውሉ
 • ጨረታው ማክሰኞ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በኩባንያው የአነስተኛ ተሸከ ርካሪዎች ማቆያ ግቢ ውስጥ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
 • ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
 • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ተሽከርካሪ የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መነሻ ዋጋቸው ከብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በታች ለሆኑ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋቸው በሚከተለው ዝርዝር መሰረት እንዲሆን ወስኗል፡፡

የጨረታ መነሻ ዋጋ                           ማስያዣ

ከብር 1,000.00 በታች…………………………………………….ብር … 200.00

ከብር 1,001.00 – 2,000.00………………………………………ብር …..500.00

ከብር 2,001.00 – 4,000.00………………………………………ብር .….800.00

ከብር 4,001.00 – 14,999.00…………………………………..…ብር ..1,000.00

 • ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናል፡፡ በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
 • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ፡፡
 • አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ ረቡዕ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡
 • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማስታወሻ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913-943333፣0911 784339 ይደውሉ

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (..)