ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ከዚራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለንግድ ለመኖሪያ እና ለእንግዳ ማረፊያ የሚያገለግሉ ባለ ስምንት ወለል/ፎቅ ህንፃ ገንብቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Nib-Insurance-logo-1

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 02/05/2022
 • Phone Number : 0115544999
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/08/2022

Description

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የእንግዳ ማረፊያ የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ከዚራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለንግድ ለመኖሪያ እና ለእንግዳ ማረፊያ የሚያገለግሉ ባለ ስምንት ወለል/ፎቅ ህንፃ ገንብቶ ለማከራየት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ ህንፃ ላይ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የህንፃው ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ሀ) የእንግዳ ማረፊያ፡-

የተለያየ መጠን ያላቸው 45 ክፍሎች ያሉት እና በቤዝመንት ወለል እራሱን የቻለ የመኪና ማቆሚያ ያለው የእንግዳ ማረፊያ ሲሆን በምድር ቤቱ ላይ የእንግዳ መቀበያ ያለው፣ ከ1ኛ እስከ 7ኛ ወለል ድረስ የመኝታ ክፍሎች ያሉት በ8ኛ ወለል ላይ ለተለያየ አገልግሎት ሊውል የሚችል ክፍል ያለው

ለ) የመኖሪያ አፓርትመንቶች፡-

የተለያየ ደረጃ ያላቸው ስድስት የመኖሪያ አፓርትመንቶች በህንፃው የንግድ ክንፍ የሚገኙ

ሐ) የመሰብሰቢያ አዳራሽ፡-

በህንፃው የንግድ ክንፍ ላይ የሚገኝ ከ150 ሰዎች ያላነሰ ማስተናገድ የሚችል የስብሰባ አዳራሽ፣ ሌሎች ተዛማጅ ክፍሎች እና የመናፈሻ ቦታ (TERRACE) ያለው

 1. ተጫራቾች የታደሰ እና ከጨረታው ጋር ተዛማጅነት ያለው የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የወቅቱን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬትና ሌሎች ህጋዊ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚከፈትበት የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ከንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና መስሪያ ቤት ደንበል ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1101 አዲስ አበባ ወይም ድሬዳዋ ከዚራ አካባቢ በሚገኘው የንብ ኢንሹራንስ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በማሳየት መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የእንግዳ ማረፊያውን፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን እና የመሰብሰቢያ አዳራሹን በጥቅል ወይም በተናጠል መጫረት ይችላሉ::
 4. በጥቅል የሚጫረቱ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ለእንግዳ ማረፊያ፣ ለመኖሪያ አፓርትመንቶች እና ለመሰብሰቢያ አዳራሽ በማለት በግልፅ በስም በመለየት መቅረብ አለበት፡፡
 5. ጨረታው የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋናው መስሪያ ቤት ደንበል ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1101 ይከፈታል፡፡
 6. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው የንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና መስሪያ ቤት ደንበል ሲቲ ሴንተር 11ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1101 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
 8. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ ቁጥር 011 5 54 49 99/011-5-54-01-76

ፋክስ ቁጥር 011 5 50 42 95

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ