ቡና ባንክ ለብድር ማካካሻ የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 02/05/2022
- Phone Number : 0111580879
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/19/2022
Description
የመኖሪያና ቤቶች እና ተሸከርካሪ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BIB/PFMD/001/2022
ቡና ባንክ ለብድር ማካካሻ የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የባለንብረት ስም | የቦታው ስፋት | ለጨረታ የቀረበው ንብረት የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | |
ከተማ | ወረዳ/ቀበሌ/የቤት ቁጥር | ||||
1 | አቶ አትርሴ ወ/ሚካኤል አጮ | 364 ካ.ሜ (መኖሪያ ቤት) | ቦንጋ ከተማ | በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ አውራዳ ቀበሌ | ብር 381,907.78 |
2 | አቶ ፍስሃ አዱ ወርቁ | 200 ካ.ሜ
(መኖሪያ ቤት) |
ሱሉልታ ከተማ | ሱሉልታ ከተማ ቀበሌ 01 | ብር 847,907.89 |
3 | አቶ ግርማ ደለሳ ቢቂላ | 200 ካ.ሜ
(መኖሪያ ቤት) |
ሱሉልታ ከተማ | ሱሉልታ ከተማ ቀበሌ 01 | ብር 1,820,243.84 |
4 | አቶ አክሊሉ ያረጋል ተፈራ | ቼቭረሌት የመስክ ተሸከርካሪ | አ.አ 02-00257 | የሻንሲ ቁጥር 1GNDT137R2145750 | ብር 279,450.00 |
የጨረታ መመሪያዎች
- ንብረቶቹን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቡና ባንክ አራት ኪሎ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ ሥላሴ ቅርንጫፍ ጎን በሚገኘው የአስተዳደርና ሎጀስቲክ ዋና ክፍል ቢሮ ወይም ቤቶቹ በሚገኙባቸው ከተሞች በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ዘውትር በስራ ሰዓት በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ጨረታው የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት 4፡20 ሰዓት የጨረታ ሰነድ በገዙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ መኖሪያ ቤት እና ተሸከርካሪ የጨረታ መነሻውን አስር በመቶ(10%) በቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ወይም “Bunna International Bank S.C” ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸውን ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ንብረቶቹን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አድራሻ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑና ከሊዝና ታክስ ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎች የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ
የባለራዕዮች ባንክ!!
0111580879/0111261901