የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዕዳ ማካካሻነት ከተረከባቸው ንብረቶች መካከል በድሬደዋ ከተማ የሚገኘውንና በቀድሞው ሰለንዳዋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር ስም የሚታወቀውን የፋብሪካ ህንፃና የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎች በድርድር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial-Bank-of-Ethiopia-Logo-5

Overview

  • Category : Industry & Factory Foreclosure
  • Posted Date : 02/05/2022
  • Phone Number : 0113852139
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 02/28/2022

Description

የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዕዳ ማካካሻነት ከተረከባቸው ንብረቶች መካከል በድሬደዋ ከተማ  የሚገኘውንና በቀድሞው  ሰለንዳዋ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር ስም የሚታወቀውን  የፋብሪካ ህንፃና የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎች በድርድር ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ፋብሪካውን ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ድርጅቶችና ግለሰቦች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 የስራ ቀናት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል በአካል በመገኘት ፕሮፖዛላችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ፕሮፖዛሉም  ዝርዝር የስራ ዕቅድ /Business Plan/ ፣ የገዢውን ድርጅት አጠቃላይ  የንግድ እንቅስቃሴ የሚያሳይ /profile/  ፣ የምትገዙበትን የገንዘብ መጠን፣ በብድር የምትገዙ ከሆነ የቅድመ ክፍያ ፕርሰንት መጠን፣ የአከፋፈል ሁኔታ እና ጊዜ ፣ በጥሬ ገንዘብ ማለትም በኢትዮጵያ ብር ወይም ተመጣጣኝ በሆነ የውጭ ምንዛሪ የመግዛት ፍላጎታችሁን ……. ወዘተ  ያካተተ መሆን አለበት፡፡

 

ተ.ቁ

 

የንብረቱ ዓይነት

 

አድራሻ

 

የቦታው ስፋት

 

የካርታ ቁጥር

 

የንብረቱ ወቅታዊ ግምት

 

1

የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ህንፃ ድሬድዋ

ቀበሌ 02

180,000 ካሬ ሜትር /18 ሄክታር/ መል/ሊ/2618 384,923,897.11
2 የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ማሽነሪዎች ድሬድዋ      ቀበሌ 02                163‚222,925.58
                          

                                                                           ጠቅላላ  ድምር

548146822.69

ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባንኩ በዕዳ ማካካሻነት የተረከባቸው ንብረቶች አስተዳደር ክፍል ከሳር ቤት ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከሳልቫቶሬ ዴቬታ የእንጨትና ብረታ ብረት ስራ ጀርባ ወይም  ከዋናው መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ወልደማርያም ህንፃ ቢሮ ቁጥር 11 በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ወይም በስልክ ቁጥሮች 0113-85-21-39 ወይም 091148/29/14 በመደወል ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ የድርድር ሽያጩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡