ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ያገለገሉ ፎርድ ኤቬረስት ስቴሽንዋገን ፡ ፎርድ ሬንጀር ፒክ አፕ፡ ቶዮታ ሃይሉክስ ፒክ አፕ እና ጂሊ ሴዳን መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 02/07/2022
 • Phone Number : 0114653043
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/21/2022

Description

ያገለገሉ መኪኖች ሽያጭ ጨረታ

ቶታል ኢነርጂስ  ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ያገለገሉ  ፎርድ ኤቬረስት ስቴሽንዋገን ፡ ፎርድ ሬንጀር ፒክ አፕ፡ ቶዮታ ሃይሉክስ ፒክ አፕ እና ጂሊ ሴዳን   መኪኖችን  በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ  ከጥር 30  ቀን 2014 እስከ የካቲት 14 ቀን 2014  ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ መኪኖችን ጎተራ በሚገኘው  የድርጅቱ ቅጥር ግቢ ሄደው ማየት እና  የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ / ብር በመክፈል ከድርጅቱ ግዢ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ ፡፡

 • ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ፤  ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ  ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች በሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT 15%/ መጨመር አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም P.O. ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • መኪኖቹ የሚሸጡት ባሉበት ሁኔታ ነው፡፡
 • ተጫራቾች አድራሻቸውን (ስም ፡ ስልክ ቁጥር የመሳሰሉትን ) የሚወዳደሩበትን የመኪና አይነት በፖስታው ላይ በግልጽ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታውን ሰነድ መመለሻ መጨረሻ ቀን የካቲት 15  ቀን 2014  ዓ.ም እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ  ሲሆን የጨረታውን ሰነድ በድርጅቱ እቃ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 • አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በተገለፀለት በ 5 ቀን ውሰጥ ሙሉውን ዋጋ መክፈል ግዴታ አለበት ይህ ካልሆነ ግን ያስያዘው ገንዘብ በቅጣት መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
 • ገዢው (የጨረታው አሸናፊ) ያሸነፈውን መኪና መረከብ የሚችለው የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) በስሙ አዙሮ  እና የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ገብቶ ሲጨርስ ብቻ ነው፡፡
 • መኪናውን በተመለከተ ፡ የባለቤትነት ስም ማዞር : በተጨማሪነት የሚጠየቅ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ክፍያዎች ; እንዲሁም ማናኛውምን የመንግስት አካል የሚጠይቃቸው ወጪዎችን ገዢው ወይም የጨረታው አሸናፊ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
 • አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን መኪና ከድርጅቱ ጊቢ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ያነሳል፡፡
 • ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ  የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ዋናው መስሪያ ቤት አድራሻ  ንፋስ ስልክ ከ/ከ ከጎተራ ማሳለጫ ወረድ ብሎ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ላይ ቡና ቦርድ  ሙለጌ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 65 3044 or 0114668025 በስራ ሰዓት በመደወል መጠየቅ ይቻላል

ቶታ ኢነርጂስ  ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ .