የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የሱፍ የምግብ ዘይት ፤ ፓስታና ማካሮኒ ፤ትራስ፤ ብርድልብስ፤ አንሶላ፤ ፎጣ እና ደብተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 02/09/2022
- Phone Number : 0113692647
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/22/2022
Description
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 015/14
ድርጅታችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ማዕከላቱ በኩል ለተጠቃሚው ማህበረሰብ የሚያሰራጨውና በኢትዮጵያ የወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ
- የሱፍ የምግብ ዘይት (CES17-2014) ፤ ፓስታና ማካሮኒ (ES 1055:2005) ፤ትራስ፤ ብርድልብስ፤ አንሶላ፤ ፎጣ እና ደብተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ፤
- ለሱፍ ዘይት አቅርቦት መወዳደር የሚችሉት የሀገር ውስጥ አምራቾች፤ በፍራንኮ ቫሉታ ወይም በዲያስፖራ የሒሳብ ቁጥር ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ፍቃድ ያላቸውና በሀገሪቱ የወጡትን መስፈርቶች በሙሉ የሚያሟሉ እና የግል አስመጪዎች መሆኑ ይጠበቅባቸዋል፤
- ለደብተር አቅርቦት መወዳደር የሚችሉት የሀገር ውስጥ አምራቾች እና አስመጪዎች መሆኑን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለተቀሩት ምርቶች መወዳደር የሚችሉት የሀገር ውስጥ አምራቾች መሆኑ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት እና ሌሎች አስፈላጊ ህጋዊ ሠነዶች ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ መጠንን ጨምሮ በጨረታ መመሪያው ላይ የተቀመጡትን ግዴታዎች በሙሉ መወጣት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-26-47/69-24-39