አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 02/09/2022
- Phone Number : 0115570075
- Source : Reporter
- Closing Date : 03/15/2022
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተገለፁትን ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለ በተሰጠው ስልጣንና ውክልና መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
ተ.ቁ. | የተበዳሪው ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረት አስያዥ ስም | የቦታ አገልግሎት | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀን | የጨረታ ሰዓት | ||
ከተማ | ክፍለ ከተማ | ቀበሌ /ወረዳ | ||||||||||
1 | ጎልደን ኤን ብሉ ትሬዲንግ እና ትራንሰፖርት ኃ/የተ/የግ/ማ/ | ሻላ አካባቢ
|
ተበዳሪው | ለንግድ | አ/አ | ቦሌ | 03 | AA000060304379 | 2024 | 22,000,000 | 6-7-14 | 4፡00-5:00 |
2 | ዘውዱ አጥናፉ | መሃል አራዳ | ተበዳሪው እና ገነት ደጉ | ለመኖርያ | አ/አ | ቦሌ | 16 | ቦሌ16/110/2260/00 | 500 | 4,200,480 | 6-7-14 | 5:00-6:00 |
3 | ብርሃኑ አሌ | ሾኔ | ተበዳሪው | ለመኖርያ | ሾኔ | – | – | ሾ/መ/421/2008 | 350 | 800,000 | 6-7-14 | 5:00-6:00 |
4 | አህመድ ዳውድ | ሀሮማያ | ተበዳሪው | ለመኖርያ | ሀሮማያ | – | – | 167/92 | 115.55 | 533,570 | 6-7-14 | 5:00-6:00 |
5 | ዋን ፎር ኦል ማይኒንግ እና ኳየሪንግ ኃላ. የተ. የግል ማ. | እንደራሴ | አደባ ነጋሳ | ጅምር G+2 ለመኖርያ | ሱሉልታ | – | – | BNMLM/SUL/134/06 | 200 | 2,000,000 | 7—7-14 | 5፡00-6፡00 |
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳው ወይም ሕጋዊ ወኪሉ፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በባንኩ 11ኛ ፎቅ በሚገኘው የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ከተራ ቁጥር 3-5 የተዘረዘሩት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ንብረቶቹ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ግን ባንኩ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን ጨረታው ከተደረገበት ቀን ቀጥሎ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለተጫራቹ ያሳውቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከባንኩ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ከመኖሪያ ቤቶች ውጭ ባሉ ንብረቶች ሽያጭ ላይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የሚታሰብ ሲሆን ሁሉንም ንብረቶች በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያ ገዢ ይከፍላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡፡- ሻላ አከባቢ ቅርንጫፍ 0116-67-38-20፡ መሃል አራዳ ቅርንጫፍ 0111-11-92-26፣ሾኔ ቅርንጫፍ 046-553-09-08፣ ሀሮማያ ቅርንጫፍ 025-661-04-67፣ እንደራሴ ቅርንጫፍ 0115-57-62-70 ወይም የሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 0115-57-00-75 ብሎ መደወል ወይም በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዋሽ ባንክ