አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማኅበር በሻሸመኔ ከተማ ቡልቻና ቀበሌ ለቢሮ እና ለመጋዘን አገልግሎት ሲገለገልበት የነበረውን 2040 ካሬ ሜትር ቅጥር ግቢ ውስጥ ያረፈ ቢሮ እና መጋዘን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ።

Ambo-Mineral-Water-S.c.-Logo

Overview

 • Category : Warehouse & Store
 • Posted Date : 02/09/2022
 • Phone Number : 0911939397
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 03/01/2022

Description

 የመጋዘን እና የቢሮ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማኅበር በሻሸመኔ ከተማ ቡልቻና ቀበሌ ለቢሮ እና ለመጋዘን አገልግሎት ሲገለገልበት የነበረውን 2040 ካሬ ሜትር ቅጥር ግቢ ውስጥ ያረፈ ቢሮ እና መጋዘን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ። ተጫራቾች ንብረቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሻሸመኔ ከተማ ቡልቻና ቀበሌ በአካል ተገኝተው ንብረቱን መመልከት ይችላሉ ፡:

ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ አመልካቾች በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

 1. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) 100,000 (መቶ ሺህ) ብር ከሚያቀርቡት የተፈረመበት የዋጋ ማቅረቢያ ጋር ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ሳጥን አዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት (ከታች በተገለፀው አድራሻ) 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
 2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ
 3. ሲፒኦ በአምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ስም ብቻ መዘጋጀት አለበት ።
 4. ተጫራቾች ለተጫረቱት ዋጋ ቫትን አካቶ ማቅረብ አለባቸው ካልተገለፀ ግን የቀረበው ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንደተሰጠ ይቆጠራል ፡፡
 5. ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት የስራ ቀናት ወስጥ በመጨረሻው ቀን አሰክ ቀኑ 8 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘዉ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በማቅረብ አንዲወዳደሩ አክስዮን ማህበሩ ይጋብዛል
 6. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታዉ በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል።
 7. አሸናፊነቱ የተረጋገጠ ተጫራች የአሸነፈበትን የቢሮ እና የመጋዘን ዋጋ በሁለት ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ ማስገባት ይኖርበታል ።
 8. ከባለቤትነት ስም ዝውውር ጋር የተያያዙ የታክስ ክፍያዎችን እና ሌሎች የ አገልግሎት ወጪዎቸን የጫረታው አሸናፊ ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል ።
 9. ከላይ ያሉትን ማናቸውንም መስፈርቶች አለመሟላት ከጨረታው ውድቅ ያስደርጋል ፡

መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃዎችን ከድርጅቱ ግዢ ክፍል በሚከተለው ቁጥር ማግኘት ይችላሉ 0911939397/0911511943 ወይም በአካል በመገኘት መረዳት አንደሚችሉ አናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፡አክስዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡